Popular Posts

Follow by Email

Saturday, October 13, 2018

የመልካም ነገር ጀማሪ


በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 16
በህይወታችሁ ምንም መልካም ነገር ካያችሁ እግዚአብሄር ስለጀመረው ብቻ ነው፡፡ ሰው በሰውነቱ በራሱ የሚጀምረው መልካም የእግዚአብሄር ነገር የለም፡፡
ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። የማርቆስ ወንጌል 10፡18
እውነተኛ መልካም ነገር በህይወታችሁ ካለ እግዚአብሄር ጀምሮታል ከእግዚአብሄ ተቀብላችሁታል፡፡ ለመልካም ነገር ልባችን ከተነሳሳ በምንም ነገር ስለበለጥን ይሆን እግዚአብሄር ልባችንን ስላነሳሳ እግዚአብሄር ስላቀበለን ነው፡፡  
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡7
እግዚአብሄር በህይወታችሁ መልካም ነገር ማድርግ ሲፈልግ ሃሳብን ይበእኛ ውስጥ ይዘራል፡፡ እግዚአብሄር በነገሮች ከመባረኩ በፊት ለነገሮች ባለ መነሳሳት ይባርካችኋል፡፡ እግዚአብሄር በምንም ነገር ከመባረኩ በፊት የሚባርካችሁ በመሳሳት ነው፡፡
የእግዚአብሄር የመጀመሪያ በረከት መነሳሳት ነው፡፡ በውስጣችሁ አስባችሁ የማታውቁትን ሃሳብ የሚሰጣችሁ እግዚአብሄር ነው፡፡ ይቻላል ብላችሁ አስባችሁ የማታውቁትን ነገር እንደሚቻል ድፍረትን የሚሰጣችሁ እግዚአብሄር ነው፡፡
የረሳችሁት ወይም አስባችሁ የማታውቁትን ሃሳብ ይቻላል ብሎ ያነሳሳችኋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበልን ሁላችን የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጣችን ይኖራል፡፡ በውስጣችን የሚኖረው የእግዚአብሄር ህይወት በህይወታች ሊሰራ ያለውን ነገር ለመስራት ሲንቀሳቀስ ልባችንን ያነሳሳል አብረነውም እንንቀሳቀሳለን፡፡
ስለዚህ ነው ሰው መጨነቅ የሌለበት፡፡ እግዚአብሄር የህይወታችን ባለቤት ነው፡፡ እኛ ብንምተወው እንኳን የእግዚአብሄን ነገር እንፈልግ እንጂ እግዚአብሄር አይተወውም፡፡  በህይወታችን ያለው አላማ መፈፀም እኛ ከምንፈልገውና እኛን ከሚጠቅመው በላይ እግዚአብሄር ይፈልገዋል እግዚአብሄርን ይጠቅመዋል፡፡
እግዚአብሄር መሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጀማሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ባለቤት ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #ህብረት #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment