Popular Posts

Friday, October 5, 2018

የምናጭደውን አንወስንም


የሰው ልጅ ብዙ ችግሮች የሚመጡት ማድረግ የሚችለውን ባለማድረግ ማድረግ የማይችለውን ለማድረግ በመሞከር ነው፡ሰው ማድረግ የሚችለውንና ማድረግ የማይችለውን ነገር ለይቶ ሲረዳ ያርፋል፡፡
ሰው በህይወት የሚወስንባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሰው በህይወት መወሰን የማይችልባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሰው መወሰን ከማይችለው ነገር አንዱ የሚያጭደውን የመከር አይነት መወሰን ነው፡፡ ሰው የሚዘራውን እንጂ የሚያጭደውን አይወስንም፡፡  
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7
እንክርዳድ ዘርቶ ስንዴን ለማጨድ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ያልዘራውን ለማጨድ የሚጠባበቅ ሰው በከንቱ ይመኛል፡፡
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። የያዕቆብ መልእክት 1፡16
በህይወታችን የሚበቅለው የምንዘራው ነገር ነው፡፡
መልካም ነገርን ማጨድ የሚፈልግ ሰው መልካምን ብቻ ለመዝራት መጠንቀቅ አለበት፡፡
ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡10-11
ጥበበኛ ሰው ያገኘውን ዘር አይዘራም፡፡ ጥበበኛ የሆነ ሰው የሚዘራውን ዘር በመምረጥ ያታወቃል፡፡ ጥበበኛ የሆነ ሰው መከሩን የሚያጭደው መልካመን ዘር በመዝራት ነው፡፡
ክፉ የሚዘራ ሰው መልካምን ማጨድ አይችልም፡፡ ሰው በስጋ ዘርቶ በመንፈስ ማጨድ አይችልም፡፡
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7-8
መልካምን የሚዘራ ሰው ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መልካምን ያጭዳል፡፡
በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡8-9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ክብር #ራእይ #ስጋ #ሃሳብ #የዘራውን #ያጭዳል #አትሳቱ #አይዘበትበትም #መበስበስ #ሰላም #ህይወት #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መንገድ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment