Popular Posts

Thursday, October 11, 2018

የልብ ጤንነት


እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል። የማርቆስ ወንጌል 7፡20-23
ሰው እንደሚያይ እግዚአብሄር አያይም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረው የልብ ጉዳይ ነው፡፡
ሰው ለስገጋ ልቡ ይጠነቀቃል፡፡ ሰው በምድር ላይ ብዙ አመት መኖር ከፈለገ ብዙ ጮማ ባለመብላት  ፍራፍሬን በመብላት እንቅስቃሴን በማድርግ በመሳሰሉት ለስጋ ልቡ ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡
ሰው ውጭው ምንም ጤነኛ ቢመስል ልቡ ጤነኛ ካልሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው ውጭው ጤነኛ ባይመስል ልቡ ግን ጤናማ ቢሆን ድኗል፡፡
ሰው ብዙ ጊዜ ስለ ውጫዊው ነገር በጣም ይጠነቀቃል፡፡ ስለሚለብሰው ልብስ ስለሚነዳው መኪና ስለሚኖርነት ቤት ጥራት አብዝቶ ያስባል ይጠነነቀቃል፡፡
ሰው ለምንም ነገር ከሚጠነቀቀው በላይ ለልቡ ጤንነት መጠንቀቅ አለበት፡፡
ሰው በልቡ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና እንዳይኖር አጥብቆ ልቡን መጠበቅ አለበት፡፡
የልብ ጤንነት መጓደል ከየትኛውም አስከፊ በሽታ ይልቅ ይጎዳል፡፡ እግዚአብሄርን ለመምሰል ለልባችን መጠንቀቅ ለአሁንና ለሚመጣው ዘመን ሁሉ ይጠቅማል፡፡
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡8
ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡25-28፣31
ሰው የልቡን ጤንነት ሳይጠብቅ በክርስትና እና በአገልግሎት እቋቋማለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ በምንም በምንም ብሎ የልቡን ንፅህና የማይጠብቅ ሰው በንስሃ ካልተመለሰ በህይወትም ሆነ በክርስትና አይሰነብትም፡፡ የልቡን ጤንነት የማይጠብቅ ሰው ስለሚረክስ እግዚአብሄር ሊጠቀምበት አይችልም፡፡
የከበረውን ከተዋረደው ሳይለይና የልቡን ጤንነት ከሚጎዱ ነገሮች ልቡን ሳይጠብቅ በክርስትናና በአገልግሎት ፍሬያማ ለመሆን ማሰብ መታለል ነው፡፡ የልብን ጤንንት ሳይጠብቁ በክርስትና የእግዚአብሄርን አላማ እፈፅማለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡
የልባችንን ጤንንት የምንጠብቀው በእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
ልባችንን ሊያክመን የልባችንን ጤንነት ሊጠበቅ የሚችለው ለእግዚአብሄር ቃል ህክምና ራሳችንን በሰጠን መጠን ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ወደ ዕብራውያን 4፡12-13
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡23
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ሃሳብ #መነሻሃሳብ #ልብ #ንፁህ #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment