እንዲህም
አላቸው፦ የአሕዛብ ነገሥታት ይገዙአቸዋል፥ በላያቸውም የሚሠለጥኑት ቸርነት አድራጊዎች ይባላሉ። እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ፤ ነገር ግን ከእናንተ ታላቅ የሆነ በመካከላችሁ እንደ ታናሽ፥ የሚገዛም እንደሚያገለግል ይሁን። በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ። የሉቃስ ወንጌል 22፡25-27
ስልጣን
መበለጥ መሆኑን ብናውቅ ኖሮ ብዙዎቻችን አንፈልገውም ነበር፡፡ ስልጣን ማገልገል ነው፡፡ ስልጣም መጥቀም ነው፡፡ ስልጣን መባረክ
ነው፡፡
ባለስልጣን
ህዝቡን ማገልግል ግዴታው ነው፡፡ ባለስልጣን ህዝቡን በማገልግል ውለታ እየሰራላቸው አይደልም፡፡
ከባለስልጣን
ይልቅ ህዝብ ይበልጣል፡፡ ከሚያገለግለው ይልቅ የሚገለገለው ይበልጣል፡፡ የሚያገለግለው ባለስልጣን ለሚገለገለው ህዝብ ተዘጋጀ እንጂ
የሚገለገለው ህዝብ ለሚያገለግለው ባለስልጣን አልተዘጋጀም፡፡
ባለስልጣንነት
በውሳኔ ሌሎችን ማገልገል ነው፡፡ ባለስልጣንነት ፊት በመቅደም ሌሎችን መንገድ ማሳየት ነው፡፡ ባለስልጣንነት ፊት ቀድሞ ለሌሎች
መጋፈጥ ነው፡፡
ባለስልጣንንት
ደስ የማይል ውሳኔ መወሰን ነው፡፡ ባለስልጣንነት በሌሎች መተቸት ነው፡፡ ባለስልጣንንት ወቀሳን መቀበል ነው፡፡ ባለስልጣንንት የህዝብን
ሸክም መሸከም ነው፡፡ ባለስልጣንነት ለህዝብ እድገት ሃላፊነት መውሰድ ነው፡፡
በማዕድ
የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ። የሉቃስ ወንጌል
22፡27
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ክብር #መዋረድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment