Popular Posts

Thursday, October 4, 2018

ከኤድስና ከካንሰር የከፋው በሽታ


ከኤድስና ከካንሰር የከፋው በሽታ ስል ደግሞ ምን አይነት በሽታ መጣ ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ዛሬ የምነግራችሁ በሽታ ግን ነገር ግን የነበረ በሽታ ነው፡፡ እውነት ነው ሰው ሲፈጠር ይህ በሽታ አልነበረም፡፡ እንዲያወም እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው በፍፁም ሰላምና በፍፁም ጤንነት ነው የፈጠረው፡፡
ሰው እግዚአብሄር አታድርግ ያለው ባደረገ ጊዜ በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ ከእግዚአብሄር ተለየ፡፡ ሰው ባለመታዘዙ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረውን የአባትና የልጅ ግንኙነት አጣው፡፡ ሰው ባለመታዘዙ እና በሃጢያት እስራት ውስጥ በመውደቁ ከሃጢያት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሞት በሽታ እና ድህነትና ጉስቁልና ውስጥ ወደቀ፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ለሃጢያት አልፈጠረውም፡፡ ሃጢያት በሰው ህይወት ውስጥ ከገባ በኋላ የሰው ልጅ ህይወት እንደገና ደህና ሊሆን አልቻለም፡፡
ሃጢያት እስራት ነው፡፡ ሃጢያት በሽታ ነው፡፡
የስጋ በሽታ ሰውን ያሰቃያል፡፡ የሃጢያት በሽታ ሰውን እንደሚያሰቃየው ግን ምንም አይነት አስከፊ በሽታ ሰውን አያስቃየውም፡፡ ምንም አይነት በሽታ የሰውን ስጋውን እንጂ ነፍሱን አያገኘውም፡፡  የሃጢያት በሽታ ሰውን ከእግዚአብሄር ክብር ዝቅ ያደርጋል፡፡ የሃጢያት በሽታ ግን ከሰው ስጋ አልፎ የሰውን ነፍስን ያሳምማል፡፡ የሃጢያት በሽታ ሰውን ያሰቃያል፡፡ የሃጢያት በሽታ ሰውን ያዋርዳል፡፡
የሃጢያት በሽታ የሰውን ሰላም ይሰርቃል፡፡ የሃጢያት በሽታ የሰውን ሰላም ይነሳል፡፡ የሃጢያት በሽታ ሰውን ለዘላለም ከእግዚአብሄር ይለያያል፡፡
ለብዙ በሽታዎች በሰው መድሃኒት ተግኝቶዋል፡፡ የሃጢያት በሽታን ግን ሊያክም የሚችል ምንም አይነት መድሃኒት በሰው ዘንድ የለም፡፡
የሃጢያት በሽታ የሚገኘው ስለ ሃጢያታችን በመስቀል ላይ ከሞተው ከኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሰው ከሃጢያት ሊያድነን አይችልም፡፡ ኢየሱስ ለሃጢያታችን መደሃኒት አለው፡፡ ኢየሱስን የተቀበለ ሰው የሃጢያት መድሃኒት ይቀበላል፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ለመሞት ወደ ምድር የመጣው እኛን ከሃጢያት ለማዳን  ነው፡፡
ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። የማቴዎስ ወንጌል 1፡21
ኢየሱስን እንደ አዳኙ የሚቀበል ሰው ከሃጢያት የበሽታ ሃይል ይድናል፡፡
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #ጸጋ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment