የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ የሰራን እግዚአብሄር ነው፡፡ ስለእኛ የሚያውቅው እግዚአብሄር ነው፡፡
ከእግዚአብሄር የበለጠ ስለእኛ የሚያውቅ የለም፡፡ ከእግዚአብሄር የበለጠ ራሳችንም ስለራሳችን አናውቅም፡፡
የእግዚአብሄር ፈቃድ ምንም የሚወጣለት ነገር የለም፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ፍፁም ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ፈቃድ እውነተኛውን ደስታ እንድናጣጥም ያደርገናል፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ከፍታና ዝቅታ ውጣ ውረድ ቢኖርበትም በእግዚአብሄር እይታ ደስታ የሚባለው በፈቃዱ ውስጥ የሚገኘው ደስታ ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ እውነተኛውን ደስታ የቀመሰ ሰው የለም፡፡
ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማን ነው? መጽሐፈ መክብብ 1:25
ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ ከምናገኘው ተድላ ይልቅ በእግዚአብሄ ፈቃድ የምናገኘው መከራ ይሻላል፡፡
ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። ወደ ዕብራውያን 11፡25-26
በእግዚአብሄር ፈቃፍ ውስጥ ያለ ትንሽ ነገር ከፈቃዱ ውጭ ካለ ታላቅ ነገር ይሻላል፡፡
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል። የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። መጽሐፈ ምሳሌ 15፡16-17
የእግዚአብሄርን መልካምነት የቀመሱ ሰዎች የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንጂ ምንም ቢያጓጓ ሌላን ነገር አይመርጡም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ጣፋጭነት የቀመሱ ሰዎች በፈቃዱ መኖር ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል ፈቃዱን እንጂ ሌላ አይመርጡም፡፡
ኢየሱስ የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ ፈቃድ ይሁን ያለው ለዚህ ነው፡፡
ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42
ፀሎት
እግዚአብሄር ሆይ ፈቃድህን እፈልጋለሁ፡፡ ለጊዜው ደስ ባይልም ፣ ለጊዜው የሚስብ ባይሆንም ፣ ብዙ ሰዎች የሚመርጡት ባይሆንም ነገር ግን ለእኔ ፈቃድህ ይሻለኛል፡፡ ምንም ዋጋ ቢያስከፍል ፈቃድህ ይሻለኛል፡፡ ምንም ቢያሳምም ፈቃድህን እፈልጋለሁ፡፡ በህይወቴ ሁሉ ፈቃድህ ይሁንልኝ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና
No comments:
Post a Comment