Popular Posts

Friday, October 5, 2018

ደስታችንን እንቆጥብ


እኛ ለማሸነፍ ሌላው መሸነፍ የለበትም፡፡ ይህ የምስኪንነት አስተሳሰብ ነው፡፡ ሁላችንም ማሸነፍ እንችላለን፡፡ ዲሞክራሲ የአብዛኛው (ማጆሪቲ) መሪነትና የብዙሃን ያልሆነውን ወይም የጥቂቶች (ማይኖሪቲ) መብትን ማስከበር ነው፡፡
ማንኛውም ግለሰብና ህዝብ መከበር አለበት፡፡ እንኳን የብዙ ህዝብ መሪና በብዙ ህዝብ የተወደዱ እንደ ዶ/ር ደብረፂዮን ያሉ መሪ ይቅርና ማንኛውም ግለሰብ መከበር አለበት፡፡ እያንዳንዳችን ለአገሪቱ ሃሳብ አለን ብለን እንደምናስበው ሁሉ ከእኛ የተለየ ማንኛውም ሃሳብ የሃገር ሃብት እንደሆነ ማሰብ አለብን፡፡ የእኛ ሃሳብ ጠቃሚ ንድሆነ እንደምናስብ ሁሉ የሌላውም ሃሳብ እኛ ያላየንበትን ጎን የሚጠቁምና የሚያነቃን ነገር እንደሆነ እንረዳ፡፡
ዲሞክራሲ የተለየ ሃሳብ ያለውን ሰው ማክበር ነው፡፡ ዲሞክራሲ የተለየ ሃሳብ ካለው ሰው ጋር በፍቅር አብሮ መኖር ነው፡፡ ዲሞክራሲ የተለየ ሃሳብ ያለውን ሰው መታገስ መቻል ነው፡፡
ሁላችን የተለያን ነን፡፡ አንድነት የሚፈልግ ሰው ለሌላው መጠንቀቅ አለበት፡፡ አንድነት የሚፈልግ ሰው ሌላውን መሸከም አለበት፡፡
የራስን ነገር ብቻ እየፈለጉ አንድነትን መመኘት ከንቱ ነው፡፡ ሌላውን ሳያከብሩ አንድነትን መፈለግ የማይታሰብ ነው፡፡ የሌላውን ሃሳብ ሳይሰሙ አንድነትን መመኘት የማይሆነ ነገር ነው፡፡ የሌላውን ሃሳብ በቅንነት ለማስማት ሳይዘጋጁ አንድንትን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ በሌላው ሰው ቦታ ሆነን የሌላውን ሰው ጉዳይ ማየት ካልቻልን አብረን መኖር አንችልም፡፡
የሌላውን የተለየ ሃሳብ ለመስማት መቅረብ ብስለት ነው፡፡ የሌላውን ተቃዋሚ ሃሳብ ማስተናገድ ብልህነት ነው፡፡
ሁሉ ሰው እንደ እኔ ካላሰበ ማለት ትእቢት ነው፡፡ ትእቢት ደግሞ ከማንም ጋር አያኖርም፡፡
አገሪቱ በጥሩ መሪዎች የተባረከች አገር ነች፡፡ አገሪቱ በጥሩ አክቲቪስቶች የተባረከች አገር ነች፡፡ አገሪቱ በመልካም ጋዜጠኞች የተባረከች አገር ነች፡፡ አገሪቱ በመልካም ሽማግሌዎች የተባረከች አገር ነች፡፡ አገሪቱ በመልካም ፖለቲከኞች የተባረከች አገር ነች፡፡  
ደስታችን ቆጠብ እናድርግና አገሪቱን እንዴት ተባብረን እንደምንገነባ እንመካከር፡፡ ካለመጠን መፈንጠዙን እናቁምና ለሌላው ሰው መጠንቀቅ እንጀመር፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ባለስልጣን #መቻቻል #መተባበር #መከባበር #ሙስና #ጉቦ #ፀሎት #ወታደር #ቀራጭ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment