Popular Posts

Sunday, September 9, 2018

ቀኑ ሲቀርብ

ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ወደ ዕብራውያን 10፡24-25
አዲስ አመት ሊገባ እየቀረበ ነው፡፡ በዛኑም መጠን የኢየሱስ መምጣት እየቀረበ ነው፡፡
ኢየሱስ ይመጣል፡፡
ኢየሱስ ለምምጣት ሲቃረብ ማድርግ ያለብንን ሶስት ነገሮች እንመልከት
1.       የኢየሱስ መምጣት ሲቃረብ መሰብሰባችንን ማብዛት አለብን እንጂ መቀነስ የለብንም
ሰው በተለያየ ምክኒያት መሰብሰብን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ከመፅሃፍ ቅዱስ በላይ ጠቢብ ሊሆን እይችልም፡፡ ፍቅርናና መልካም ስራን በማብዛት እግዚአብሄርን ማክበር የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ለፍቅርና ለመልካም ስራ ለመነቃቃት መሰብሰብን መተው የለብንም ይለናል፡፡ ባለመሰብስ ለፍቅርና ለመልካመ ስራ የመነቃቃት እድላችንን እናበላሸዋለን፡፡ ለፍቅርና ለመልካም ሰራ ለመነቃቃት ካልተሰበሰብን ፍቅር እና መልካም ስራ ከህይወታችን ይዳፈናል፡፡ እንዳንሰበሰብ የሚመጡብንን ተግዳሮቶች ሁሉ ተቋቁመን የኢየሱስን መገለጥ ስንጠባበቅ መሰብሰባችንን መተው የለብንም፡፡ ለፍቅርና ለመልካም ስራ ለመነቃቃት መተያየት አለብን፡፡ መሰበስበን አብልጠን ማድረግ አለብን፡፡
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ወደ ዕብራውያን 1024-25
2.     የኢየሱስ መምጣት ሲቃረብ በመጠን መኖርና መንቃት አለብን፡፡
ነገሮችን በልክ ማድረግ ሁልጊዜ ንቁ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ነገሮችን በልክ አለማድርግ ግን በነገሮች እንድንወሰድና የምድር አላማችንን እንድንረሳና አገልግሎታችንን እንድንፈፅም ያደርገናል፡፡
ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡11-14
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡5
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡13
3.       የኢየሱስን መምጣት ሲቃረብ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል መኖርን በፀጋ መማር አለብን
የኢየሱስ መምጣት ሲቃረብ በእግዚአብሄር ፀጋ ከሃጢያት በላይ የሆነ ህይወትን መለማመድ አለብን፡፡
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን መግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ወደ ቲቶ 2፡11-13
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ኢየሱስይመጣል #እንደሌባ #በድንገት #ዋጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #ህብረት #በመጠኑ #ቅድስና #ፀጋ #ራስንመግዛት #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment