Popular Posts

Saturday, September 8, 2018

መጋቢ የሚለካበት ዋነኛው የአገልግሎት መለኪያ


እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡28
መጋቢነት ወይም የቃሉ አገልጋይነት በዋነኝነት የሚለካው የሰውን መንፈሳዊ ህይወት ለመስራት ያለውን የማስተማር የመስበክና የመገሰፅ ሃላፊነት በመወጣቱ ነው፡፡ አንድ መጋቢ ክርስቶስን መውደዱና የመጋቢነት አገልግሎቱን በታማኝነት መወጣቱ የሚለካው ግልገሎቹን ባሰማራ ፣ ጠቦቶቹን በጠበቀና በጎቹን ባሰማራ መጠን ነው፡፡
ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው። ደግሞ ሁለተኛ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ፦ ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ። የዮሐንስ ወንጌል 21፡15-17
የመጋቢነት አገልግሎት የሚለካው የእግዚአብሄር ህንፃዎች ሆነው በተሰሩት ቤቶች ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ማደር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ሲያድር በሰዎች ተጠቅሞ መናገር መሄድ መፈወስ ሌሎችን ሰዎች በሁለንተናዊ መልኩ መድረስ ይፈልጋል፡፡ ፡፡
በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1 የጴጥሮስ መልእክት 2፡4-5
መጋቢ የሚለካው በሰበከው መጠን እንጂ በተለወጡ መጠን አይደለም
የመጋቢ ሃላፊነት የእግዚአብሄርን ቃል መፈለግ መኖርና በሚገባ ተዘጋጅቶ ለሚሰሙት ማስተማር ነው፡፡ ከዚግህ ውጭ መጋቢ ሃላፊነት የለበትም፡፡ የሰው መለወጥ ብዙ ሰዎችን ያካትታል፡፡ የሰው አለመለወጥ በመጋቢ ስብከት ላይ አይደገፍም፡፡ የሰማው ሰው አሰማሙ የህይወት ለውጡን ሊቀይትር ይችላል፡፡
ሰወፖች ካልተለወጡ ስብከቴ ምንድነው ችግሩ ብሎ ራሱን ማየት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን መጋቢው ለሰው አለመለወጥ ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ አይችልም፡፡ በኢየሱስ አስተምሪ የሚለወጡም የማይለወጡም ሰዎች ይኖተራሉ፡፡
በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።የማቴዎስ ወንጌል 13፡23
መጋቢ የሚለካው ወደ እርሱ የመጡትን ሰዎች ባስተማረ መጠን እንጂ በተማሩ መጠን አይደለም
ሰውን አስተማርን ማለት ሰው ይማራለ ማለት አይደለም፡፡ ማስተማር የመጋቢው ሃላፊነት ሲሆን መማር ግን የሚሰማው ሃላፊነት ነው፡፡
ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡6-7
መጋቢ የሚለካው በታማኝነት ባስተማረ መጠን እንጂ ባደጉ መጠን አይደለም
መጋቢ አገልግሎቱን የሚመዝነው በተለወጡ ሰዎች ከሆነ መቼም ሊያርፍ አይችልም፡፡ መጋቢ የሚያርፈው ማድርግ የሚችለውእና ማድረግ የማይችለውን ለይቶ ሲውቅ ብቻ ነው፡፡ መጋቢ የሚያርፈው ማድረግ የሚችለውን አድርጎ ማድረግ የማይችለውን ላለማድረግ ከመሞከር ሲያርፍ ብቻ ነው፡፡ የመስበክ ወይም የማስተማርን እንጂ የማሳደግ ሃላፊነትም የተሰጠው ብድራትንም የሚቀበል መጋቢ የለም፡፡
እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም። የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡6-8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ጥሪ #መገሰፅ #መምራት #ማሰማራት #መታገስ #መመገብ #መኮትኮት #ማሰማራት #መጠበቅ #ምሳሌ #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment