Popular Posts

Friday, September 7, 2018

የቅዱሳት ሴቶች ልብስ

ልብስ በህይወት ከሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ልብስ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ የምታስታውሱት ያልለበሰ ሰው እንዴት እንደማያምር ስታዩ ነው፡፡ ያልለበሰ ሰው ስታዩ ልብስ የስንቱን ገመና እንደሸፈነና ውብ እንዳደረገው ታዩታላችሁ፡፡
ልብስ ውበት ይጨምራል፡፡ ልብስ ሞገስ ይሰጣል፡፡
የመገዛት ልብስ
የሚታዘዝ ሰው ይስባል፡፡ ሴቶች የሚያመርባቸው የመገዛትን ልብስ ሲለብሱ ነው፡፡ ለባልዋ የምትገዛ ሴት ታምራለች፡፡ ለባልዋ የምትገዛ ሴት ውበት አላት፡፡ የሚስት ቁንጅናዋ ለባልዋ መገዛትዋ ነው፡፡ የሚስት ልብስዋ መገዛት ነው፡፡ ሚስት በውበት የምትሸለመው ለባልዋ በሁሉ ስትገዛ ነው፡፡
እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤ 1 የጴጥሮስ መልእክት 35
ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች ራሳቸውን ያስዋቡት በዚህ ዐይነት ለባሎቻቸው በመገዛት ነበርና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡5 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡24
የቅዱሳን ሴቶች የውጭ ልብስ
ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥ 1 የጴጥሮስ መልእክት 33
የውጭ ውበት የራሱ ስፍራ አለው፡፡ የውጭ ውበትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን ከውስጡ ውበት በላይ የውጭ ማጌጥ ላይ ማተኮር የለባቸውም፡፡ ውበት የውጭው ብቻ አይደለም፡፡ እንዲያውም ዋናው ውበት የውጭው ውበት አይደለም፡፡ የውጭው ውበት በትንሽ ነገር ይለወጣል፡፡ የውስጡ ውበት ግን ትህትናን መሰጠትንና የዋህነትን ይጠይቃል፡፡ የውጭው ውበት የውስጡን ዋናውን ውበት የሚደብቅ አታላይ ነው፡፡ የውጭው ውበት ጊዜያው ነው ያልፋል ይጠፋል፡፡ የውስጡ የከበረው እግዚአብሄርን የመፍራት ውበት ከውጭው ውበት እጅግ ይበልጣል፡፡  
ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። መጽሐፈ ምሳሌ 31፡30
የቅዱሳን ሴቶች የልብ ልብስ
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።1 የጴጥሮስ መልእክት 34
የውጭው ልብስ እንደ ውስጡ ልብስ በእግዚአብሄር ፊት የከበረ አይደለም፡፡ ምንም ውድ ቢሆን የውጪው ልብስ እንደውስጡ የልብ ልብስ ዋጋው እጅግ የከበረ አይደለም፡፡ የውጪው ልብስ እንደ ውስጡ የልብ ልብስ የማይጠፋ አይደለም፡፡ የልብ ልብስ ወርቅ እና የከበረ ልብስ አይለብስም፡፡ የልብ ልብስ የሚለብሰው የዋህነትና ዝግተኝነትን ነው፡፡ የሰው ልብ የሚያጌጠው በየዋህነትና በዝግተኝነት የመንፈስ ልብስ ነው፡፡ የውጭው ውብት ማንም የሚያውቀው ነው፡፡ የውስጡ ውበት ግን ዋጋውን የሚለየው የከበተ ሰው ብቻ ያውቀዋል፡፡ በውጭው ውበት ማንም ይሳባል፡፡ በውስጡ ውበት ግን የከበረ ሰው ብቻ ዋጋውን የሚያውቅው ሰው ይሳባል፡፡
የቅዱሳን ሴቶች የህይወት ልብስ
እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1 የጴጥሮስ መልእክት 31-2
የልብ ልብስ የማይማርከው ሰው የለም፡፡ የልብ ልብስ ይናገራል፡፡ የልብ ልብስ ካለ ቃልና ካለ ንግግር ስለ እግዚአብሄር መልካምነት ይናገራል፡፡ ሰው የሚወደውና የማይወደው የልብስ ስታይል አለ፡፡ ሰው የሚወደውና የማይወደው አለባበስ አለ፡፡ የልብን አለባበስ የዋህነትን ግን የማይወደው እና የማይማረክለት ሰው ከሰማይ በታች አይኖርም፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። የዮሐንስ ወንጌል 13፡35
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ውበት #ቁንጅና #ደምግባት #የዋህ #ዝግተኛ #ሽልማት #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment