Popular Posts

Thursday, September 27, 2018

የሚድነው ሁሉም ሰው ያልሆነው ለምንድነው ?


እግዘኢአብሄር ለሰው ልጆች መዳን የሚያስፈልገውን የሃጢያት እዳ ሁሉ በኢየሱስ በኩል እንዲከፈል ቢያደርግም እውነታው ግን ሁሉም ሰው አይድንም፡፡
ሁሉም ሰው ይድናል ብሎ እየተጠባበቀ ያለ ሰው ካለ ተሞኝቷል፡፡ ሁሉም ሰው አይድንም፡፡
የሚድነው እግዚአብሄር ያዘጋጀለትን የመዳኛ መንገድ ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስን ያልተቀበለ ሰው መዳን አይችልም፡፡
የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12-13
ሰው ሁሉ ኢየሱስን ተቀብሎ መዳን ቢችልም ኢየሱሰን የማይቀበለ ሰው ግን አይድንም፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡36
ኢየሱስን ያልተቀበለ ሰው ሃጢያቱ ለዘላለም ከእግዚአብሄር ይለየዋል፡፡ ኢየሱስን ያልተቀበለ ሰው ለሃጢያቱ የተከፈለውን እዳ ለእኔ ነው ብሎ ስላለተቀበለ እስከ እዳው ይኖራል፡፡
ለእግዚአብሄር ፍቅር ምላሽ ያለሰጠ ሰው ከዚህ ወዲያ መስዋእት አይቀርለትም፡፡
ብዙ የመዳኛ መንገዶች የሉም፡፡ መንገዱ አንድ ነው፡፡
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡6
በኢየሱስ ያልዳነ በማንም ሊድን አይችልም፡፡
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋርያት ሥራ 412
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment