Popular Posts

Sunday, September 30, 2018

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 109-10
ኢየሱስ እኛን ከሃጢያት ባርነት ለማዳን ነፍሱን ሰጥቷል፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት በእግዚአብሄርና በእኛ መካከል ያለውን ጠላትነት አስወግዷል፡፡
መዳን ታላቅ ዋጋ ቢከፈልበትም እኛ ግን ለመዳን ምንም ዋጋ መክፈል የለብንም፡፡ ማድረግ ያለብን አንድ ነገር ይህን የመዳን ስጦታ አምነን መቀበል ብቻ ነው፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡8-9
ማንም ሰው ላለመዳን በቂ ምክኒያት ሊኖረው እስከማይችል ድረስ  እግዚአብሄር መዳንን ቀላል አድርጎታል፡፡
ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡6-7
መዳን ሩቅ አይደለም፡፡ መዳን ለሚፈልግ ሰው መዳን እጅግ ቅርብ ነው፡፡
ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡8
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9-10
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment