Popular Posts

Wednesday, September 5, 2018

በአዲሱ አመት 100 % አስተማማኝ የተመሰከረለት አዋጪ የኢንቨስትመንት እድል



ሰዎች ብልሆች ናቸው፡፡ ሰዎች በአንድ ድርጅት ወይም ንግድ ላይ መዋእለ ኑዋያቸውን ከማፍሰሳቸው በፊት ስለ ንግዱ በሚገባ ያጠናሉ፡፡ ሰዎች በአንድ ድርጅት ላይ ኢንቨስት ከማድረጋቸው በፊት በዘርፉ የተሻለ እውቀት ካላቸው ሰዎች ጋር ይመካከራሉ፡፡
አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የሰዎችን በጥሩ ድርጅት ላይ ኢንቨስት የማድረግና ከፍተኛ ትርፍ የማግኘት ፍላጎት በመረዳት ይህ ያተርፋል ይህ አያተርፍም በማለት ሰዎችን ያማክራሉ፡፡
እንደዚህም ሆኖ የትኛውም ኢንቨስትመንት 100 %  አስተማማኝ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ሁልገዚ 100 % አስተማማኝ ስለሆነ ኢነቨስትመንት እንመልከት፡፡  
1.      አዋጭ ኢንቨስትመንት
በኢንቨስትመንት ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኝ ኢንቨስትመንት ሁል ጊዜ ተመራጭነት አለው፡፡ ሰው ገንዘቡን ባንክ ቢያስቀምጠው ከሚያገኘው ገንዘብ ያነሰ የሚያስገኝን ኢንቨስትመንት አይፈልግም፡፡ ሰው ለኢንቨስትመንቱ ጥሩ ምላሽ ይፈልጋል፡፡
ከዚህ አንፃር የእግዚአብሄር መንግስት ኢንቨስትመንት ከኢንቨስትመንቶች ሁሉ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ያስመሰክራል፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ኢንቨስትመንት በሁሉም የህይወታችን ክፍል የእግዚአብሄርን አብሮነት የሚያመጣልን በህይወት የሚያትረፈርፈን በሰማይም በምደርም አትራፊ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ (ዮሃንስ 10፡10)
ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡38
ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። የማቴዎስ ወንጌል 19፡29
2.     አስተማማኝ ኢንቨስትመንት
ኢንቨስትመንት አዋጭ ቢሆንም አዋጭነቱ ለጊዜው ሆኖ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ምን እንደሚሆን የማይታወቅ ከሆነ የተሻለ ተመራጭ ኢንቨስትመንት አይሆንም፡፡ በዚህ መልኩ የእግዚአብሄር መንግስት ኢንቨስትመንት አዋጭ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም የተረጋገጠ ኢንቨስትመንት ነው፡፡
እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ፦ በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤ ወደ ዕብራውያን 6፡13-14
ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤ወደ ዕብራውያን 6፡17-18
3.     ለረጅም ጊዜ የቆየ ዘላቂ ኢንቨስትመንት
አንድ ኢንቨስትመንት አዋጭም አስተማማኝም ሆኖ ነገር ግን ዘላቂ ካልሆነ አይመረጥም፡፡ አንድ ኢንቨስትመንት በቀጣይነት እና በአትራፊነት ለረጅም ጊዜ መቆየቱ ይበልጥ ተፈላጊ እንዲሆን ያድርገዋል፡፡
ከዚህ እንጻር የእግዚአብሄር መንግስት ኢንቨስትመንት ወደር የለውም፡፡ በዘመናት ከእግዚአብሄ ጋር የነገዱ ሰዎች ሁሉ ሲወጡ እግዚአብሄር መልካም አብሮ ሰራተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም የንግድ አጋር ነው ብለው ይመሰክሩለታል፡፡ 
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ወደ ዕብራውያን 12፡1-2 
4.     ኢንቨስርትመንቱን የደገፈው ሰው ታማኝነት 
ኢንቨስትመንቱን እንዲመረጥ ወይም አንዳይመረጥ ኢንቨስትመንቱን የመከረውና የደገፈው ሰው ታማኝነት ወሳኝ ነው፡፡ ኢንቨስትመንቱን የደገፈው ሰው ይበልጥ ታማኝ በሆነ ቁጥር ኢንቨስትመንቱ ይታመናል፡፡
አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። የማቴዎስ ወንጌል 25፡24-25
ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤ ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤ ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡11-13

5.     ኢንቨስትመንቱ የሚጠይቀው መጠን ተግባራዊነት
ኢንቨስትመንቱ አዋጭ ሆኖ ፣ ኢንቨስትመንቱ አስተማማኝ ሆኖ ፣ ኢንቨስትመንቱ በረጅም ጊዜ በመፅናቱ ተመስክሮለት ኢንቨስትመንቱን የደገፈው ሰው ታማኝ ሆኖ እንኳን ኢንቨስትመንቱ የሚጠይቀው ኢንቨስትመንት ከአቅም በላይ ከሆነና ተግባራዊ ካልሆነ ኢንቨስትመንቱ ለማንም አይጠቅምም፡፡  
የእግዚአብሄር መንግስት ኢንቨስትመንት ግን ለሁሉም ሰው ተግባራዉ ሊሆን የሚችል ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ማንም ያለውን ይዞ የሚመጣበት ራስን መስጠት ብቻ የሚጠይቅ ተመጣጣኝ ኢንቨስትመንት ነው፡፡
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። የማቴዎስ ወንጌል 11፡28-30
ይህን ሁሉ ካጠና ሰው በኋላ መወሰንና በተግባር መተርጎም አለበት እንጂ ምንም መዋእለ ንዋዩን ሳያፈስ ስላለው እውቀት ብቻ ከኢንቨስትመንት ተጠቃሚ የሚሆን ሰው የለም፡፡
ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ። ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት። የማቴዎስ ወንጌል 13፡44-46
በእግዚአብሄር መንግስት ሰው ባለው ገንዝብ መጠን ሳይሆን በመልካም ስራ ላይ ኢንቨስት ያደረገው ገንዘብ እና ሃብት ብቻ እንደ ኢንቨስተር አትራፊ የሚያደርገው፡፡
እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡18-19
ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡19-21
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አስተማማኝ #አትራፊ #አዋጪ #ኢንቨስትመንት #ገቢ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment