Popular Posts

Saturday, September 1, 2018

የሳኦልና የዳዊት የህይወትና የአገልግሎት ልዩነቶች - ክብርን ከሰው መፈለግ

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው የተፃፈ ሰዎች ህይወት መልካም ስራቸውን እንድንከተልና ከስህተታቸው እንድንማርና ስህተታቸውን እንዳንደግመው ያስተምሩናል፡፡
የመፅሃፍ ቅዱስ ታሪኮች እኛን ከክፋት ድነን መልካምን እንድናደርግ ሊገስፁን ተፅፏል፡፡
ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡11
ዳዊት በዘመኑ ስህተቶችን ሰርቶዋል፡፡ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ እንደ ልቤ ተብሎ በእግዚአብሄር በራሱ ደግሞ ተመስክሮለታል፡፡
እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 13፡22
ዳዊት እንደልቤ የተባለበት ምክኒያት ስህተት ሲሰራ በእግዚአብሄር ፊት ራሱ ስለሚያዋርድ ነው፡፡
ዳዊት በዘመኑ ስላልሰራው ሃጢያት እግዚአብሄር በነቢዩ ናታን አማካኝነት ሲገስፀው
ዳዊት ችግሩን ከሌላ ሰው ጋር አላገናኘውም፡፡ ዳዊት ችግር አለብህ ሲባል አንተም ችግር አለብህ ብሎ የፉክክር ነገር አላደረገውም፡፡ ዳዊት ችግር አበለብህ ሲባል እኔ ችግር የለብኝም ብሎም አልካደም፡፡ ዳዊት ችግሩን ፊት ለፊት የመጋፈጥ ድፍረት ነበረው፡፡ ዳዊት ችግሩን መጋፈጥ እርሱን እንደሚጠቅመው ሃጢያቱን ነቅሎ አንደሚጥለለት አምኖዋል፡፡ ዳዊት ይህን ያህል ከጌታ ጋር መጥቼ አሁን እንዴት ንስሃ እገባለሁ አላለም፡፡ ዳዊት ንጉስ ነኝ ብሎ ራሱን አላኩራራም፡፡ ዳዊት እግዚአብሄ እንዳከበረውና እንዳነገሰው ያውቃል እግዚአብሄን ለመስማትና ለመታዘዝ እንዲሁም ለእግዚአብሄር ሁሌ ለመኖር ወስኗል፡፡
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ። መዝሙረ ዳዊት 51፡2-4
ሰው ከሃጢያቱ የሚድነው ሃጢያቱን ሲሸፍን ሳይሆን ሲናዘዛትና ሲተዋት ብቻ ነው፡፡
ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል። መጽሐፈ ምሳሌ 28፡13
ያመነበትንና የሾመውን እግዚአብሄርን እንጂ ሰውን እንዳልበደለ ያስባል
ዳዊት በሃጢያት ሲወቀስ ነገሩን ከሰው ጋር አላገናኘውም፡፡ ዳት ሲወቀስ ነቢዩ ስለማይወደኝ ነው በማለት ነፃ የመውጣት እድሉን አላባከነውም፡፡ ዳዊት ሲወቀስ ነገሩን መንፈሳዊ በማድረግ ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያበላሽ በማወቅ ንስሃ ለመግባት ኣ ህይወቱን ለማስተካከል ደስተኛ ነበር፡፡
ሳኦል ግን ነገሩን ያገናኘው ከእግዚአብሄር ጋር ካለው ግንኙነት ሳይሆን ከሰው ጋር ነው፡፡ ሳኦል በህዝቡ ዘንድ ብቻ እንዲከበር እንጂ ከእግዚአብሄር ስለሚመጣው ክብር ግድ የለውም ነበር፡፡ ሳኦል የሰውን ድጋፍ እንጂ የእግዚአብሄርን ድጋፍ አልፈለገም፡፡ ሳኦል ለስሙ እንጂ ከእግዚአብሄር ጋር ላለው ግንኙነት መበላሸት አልተጨነቀም፡፡
እርሱም፦ በድያለሁ፤ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት፥ እባክህ፥ አክብረኝ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15፡30
ዳዊት ግን ለውጭው ስርአት ሳይሆን ለልቡ ንፅህና ያስብ ነበር፡፡ ዳዊት ግን በህዝቡ ስላው ክብር ሳይሆን በእግዚአብሄር ስላለው ክብር ያስባል፡፡
አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። መዝሙረ ዳዊት 5110-12
ዳዊት ሃሳቡ ሰው እንዲያደንቀው ሳይሆን የእግዚአብሄር መንፈስ እንዳይለየው ነበር፡፡ ዳዊት ህልውናውን እንዳያጣው የሚያስከፍለውን ሁሉ ለመክፈል ራሱን በእግዚአብሄር ፊት የሚያዋርድ እውነተኛ ሰው ነበር፡፡
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም። መዝሙረ ዳዊት 168
ሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። መዝሙረ ዳዊት 1611
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #መዳን #እምነት #እንደልቤ #ንፁህልብ #ማዋረድ #ትህትና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

No comments:

Post a Comment