Popular Posts

Monday, September 24, 2018

ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም

ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
የተለያዩ እድሎች በየጊዜው ይመጣሉ፡፡ በህይወታችን እድሎች መምጣታቸው አይቀርም፡፡ የሚመጣው እድል ተጠቃሚ የሚሆነው ሰው ግን እድሉ ሳይመጣ ለእድሉ የተዘጋጀ ሰው ብቻ ነው፡፡ ውጤት ማግኘት ከተፈለገ እድሉ ይመጣል ብሎ አምኖ አስቀድሞ መዘጋጀት መስራትና መትጋትን ይጠይቃል፡፡
እምነት የሚያስፈልገው ሳያዩ በፊት ነው፡፡ ለወደፊት መዘጋጀት ሳያዩ ነው፡፡ ለአዩት ነገር መዘጋጀት አይቻልም፡፡ የአሁትን ነገር ማስተናገድ እንጂ ለአዩት ነገር መዘጋጀት ከንቱ ነው፡፡ ካላየሁ አላምንም የሚል ሰው ሲያይ ቢያምን ዋጋ የለውም፡፡ እስከሚያይ የማያምን ሰው ሲያይ ቢያምን ረፍዶበታል፡፡
ነፋስን ሳይጠባባቅ የሚዘራ ሰው የተባረከ ነው፡፡ ደመናን ሳይመለከት የሚዘራ ሰው ሰው በጊዜው ያጭዳል፡፡
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ነፋስ #የሚጠባበቅ #አይዘራም #ደመና #አያጭድም #የጌታፈቃድ #ይቀጣል #በብዙ #በጥቂት ##ታማኝ #ትጉህ #መክሊት #ትውልድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ሃሳብ #ገንዘብ #ጊዜ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment