Popular Posts

Wednesday, September 5, 2018

ጸሎታችሁ እንዳይከለከል


እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡7
ፀሎት የአጠቃላይ የክርስትና ህይወት አንዱ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ሰው በፀሎት ብቻ ሊያድግ አይችልም፡፡ የሰው የፀሎት ህይወቱ የሚያድገው ህይወቱ ሲያድግ ነው፡፡ የሰው የፀሎት ህይወቱ የሚያድግው በፍቅር ሲያድግ ነው፡፡
ሰው ፍቅር ፍቅር አንሶት በፀሎት ብቻ ሊበዛ አይችልም፡፡  
እግዚአብሄር የፀሎት ንግግራችንን ብቻ ሳይሆን የህይወት ፀሎታችንን ይሰማል፡፡ የራሳችንን ነገር አድርገን እግዚአብሄርን በፀሎት እንሸውደውም፡፡ ህይወታችንም የፀሎት አይነት ነው፡፡
ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡21
እግዚአብሄርን በፀሎት እወድሃለሁ ብንለው ወንድማችንን ካልወደድን እግዚአብሄር አያምነንም፡፡
ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡20
ህይወቱ የተከለከለ ሰው ፀሎቱ ይከለከላል፡፡ በህይወቱ ቸር ያልሆነ ሰው በፀሎት የእግዚአብሄርን ቸርነት አያገኝም፡፡ በህይወቱ ምህርት የሌለው ሰው የእግዚአብሄርን ምህረት አያይም፡፡ በህይወቱ ለሌላው የማይጠነቅቅ ራስ ወዳድ ሰው ይጠነቀቅልኛል ብሎ በእግዚአብሄር ላይ ድፍረት ሊኖረው አይችልም፡፡
እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ የማቴዎስ ወንጌል 6፡12
ከሰው ጋር ግንኙነቱን ለማስተካከል የማይፈልግ ትእቢተኛ የሆነ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር በትህትና ለመገናኘት አይችልም፡፡
እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡23-24
ለእግዚአብሄር ቃል የዋህ በሆንንበት መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄር ለፀሎታችን ቃል የዋህ የሚሆነው፡፡ ቃሉን ባመንነው መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄር ቃላችንን የሚየምነው፡፡ እግዚአብሄር በፀሎት የጠየቅነውን የሚያደርግልን ቃሉ የጠየቀንን ባደረግን መጠን ብቻ ነው
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7
በፀሎት ውስጥ ታላቅ ሃይል ያለ ቢሆንም በሃጢያታችን ንስሃ ካለመግባት ፣ ከኑሮዋችን አለመፈወስና በፍቅር አለመመላለስ ምክኒያት ጸሎታችን ሊከለከል ይችላል፡፡
እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። የያዕቆብ መልእክት 516
እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡7
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ልመና #እንዳይከለከል  #ቃል #መኖር #እምነት #መስማት #መታዘዝ #በቃሉመኖር #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #ሚስት #ማስተዋል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment