Popular Posts

Monday, September 17, 2018

አጥብቀህ


አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡23
ህይወት የሚወጣው ከልብ ነው፡፡ የሰው አካሄድ የሚወጣው ከልቡ ነው፡፡ የሰው አካሄድ የሚጀምረው በልቡ ነው፡፡ ሰው የሚኖረው የልቡን ሃሳብ ነው፡፡ ሰው የሚመስለው ልቡን ነው፡፡
እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል። የማርቆስ ወንጌል 7፡19-23
ልብህ ከወደቀ ትወድቃለህ
ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያውን አምላክ ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17፡26
ልብህ ከቆሸሸ ትቆሽሻለህ
ልብሳችንና ቤታችን እንዳይቆሽሽ በንፅህና እንደምንጠብቀው ሁሉ ልባችንን መጠበቅ አለብን፡፡ ቤታችንና ልብሳችን ሲቆሽሽ እንደሚያሳፍረን ሁሉ ከልብስና ከቤት መቆሸሸ በላይ ህይወታችንን ሊገድልና ሊያድን የሚችለውን የልባችንን መቆሸሽ ሊያሳፍረን ይገባል፡፡ ለሰው የሚታየው የቤታችንና የልብሳችን መቆሸሽ ከሚያሳፍረን በላይ ውሎ አድሮ በተግባር የሚታይው የልባችን መቆሸሽ ሊያሳፍርን ይገባል፡፡ ቤታችንንና ልብሳችንን ለማፅዳት ጊዜያችንን ገንዘባችንን ጉልበታችንን ከምናፈሰው በላይ የህይወት መውጫ የሆነውን ልባችንን ለማንፃት ሁለንተናችንን መስጠይት ይገባናል፡፡    
አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። መዝሙረ ዳዊት 51፡10
ልቡን የሚመረምርና ልቡን ለማጥራት የሚተጋ ሰው ከክፋት ያርፋል በህይወቱንም ፍሬያማ ይሆናል፡፡
ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡8
የሰው ሃሳብ ሰውን እንሚያረክሰው የሚበላው ምግብ ሰውን አያረክሰውም፡፡ ለምንበላው ምግብ ከምንጠነቀው በላይ ለልባችን ንፁህነት መጠንቀቅ ህይወታችንን ያድነዋል፡፡
ልብህ ከበረታ ትበረታለህ
ሰው የሚበረታውምን የሚደክመውም በልቡ ነው፡፡ ሰው በልቡ ከበረታ ይብረታል፡፡ ሰው በልቡ ከደከመ ይደክማል፡፡
ሰው ህይወቱን የሚያስተካክለው በልቡ ነው፡፡ ሰው ልቡን ሳይጠብቅ ህይወቱን መጠበቅ አይችልም፡፡ ሰወ ልቡን ከተጠበቀ ህይወቱ የማይጠበቅበት ምንም ምክኒያት የለም፡፡
በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡7
በነጋውም የጠጁ ስካር ከናባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገረችው፤ ልቡም በውስጡ ሞተ፥ እንደ ድንጋይም ሆነ፤ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 25፡37
ልቡን በእግዚአብሄር ቃል ለመቃኘት ራሱን የሰጠ ሰው ህይወቱ ይቃኛል፡፡   
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
ልቡን ለመጠበቅ ቸልተኛ የሆነ ሰው ለህይወቱ ግድ የሌለው ሰው ብቻ ነው፡፡ ህይወቱን መጠበቅ የሚፈልግ ሰው አጥብቆ ልቡን መጠበቅ አለበት፡፡
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡23
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ሃሳብ #መነሻሃሳብ #ልብ #ንፁህ #ማየት #ምኞት #ንፁህ #አጥሩ #ልብ #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment