Popular Posts

Thursday, September 13, 2018

የሽማግሌ ፈተና

ሽማግሌ ማለት በህይወት ልምድ የሚሰራበትንና የማይሰራበትን የሚያውቅ ሰው ማለት ነው፡፡
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። ወደ ዕብራውያን 5፡14
የወጣት ፈተና ከልምድ ማጣትር የተነሳ የሚሰራበትንና የማይሰራበትን መንገድ ለይቶ አለማወቅ ነው፡፡ የሽማግሌ ፈተና ግን ህይወት የሚሰራበትን መንገዱን ማወቅ አይደለም፡፡ ሽማግሌ ከረጀም የኑሮ ልምድ የሚሰራበትንና የማይሰራበትን መንገድ በህይወቱ ፈትኖ ያውቀዋል፡፡ የማይሰራበትን መንገድ ሄዶበት አይቶታል፡፡ እንዲሁም የማይሰራበትን መንገድ ሄዶበት አውቆታል፡፡
የሽማግሌ ፈተና ወጣቱ የሚሄድበትን መንገድ የተሳሳት እንደሆነ እያወቀው አያስጠነቀቀው ነገር ግን ወጣቱን አላስፈላጊ ዋጋ ከመክፈል ማዳን አለመቻሉ ነው፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር ለሰው ትእዛዝ ሰጠው፡፡ እግዚአብሄር የሚበላውንና የማይበላውን በግልፅ ነገረው፡፡ እግዚአብሄር የማይበላውን ቢበላ ምን እንደሚገጥመው ሁሉ አስቀድሞ ተናገረው፡፡ እግዚአብሄር አድርግ የተባላነውቅን ካደረገ ምን እንደሚገጥምው አስቀድሞ ተናግሮታል፡፡
እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? ኦሪት ዘፍጥረት 3፡11
ሰው የራሱ ፈቃድ ያለው ተደርጎ ሰለተፈጠረ እግዚአብሄር እንደ አባትነት ከመንገር እና ከማስጠንቀቅ በላይ ከመርጫው ውጤት ከጥፋት ሊያድነው ምንም ሊያደርግለት አልቻለም፡፡
ወጣት ልጅ ተነግሮት አታድርግ የተባለውን ነገር ሲያደርግና በዚያም ውጤት ሲሰቃይ ማየት የአባትነት ህመም ነው፡፡ ልጅ ተነግሮት እንቢ ብሎ ሲሰቃትይ ሲያለቅስና ሲጎዳ ማየት የሽማግሌነት ፈተና ነው፡፡
በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥ ትላለህም፦ እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ! የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም። መጽሐፈ ምሳሌ 5፡11-13
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ለሽማግሌዎች ተገዙ የሚለው፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ በሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በትግባር ተረድተው የሚመክሩንን ሽማግሌዎችን መስማት እና እግዚአብሄርን መስይት አንድ ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ለሽማግሌዎች ተገዙ ብሎ ከእግዚአብሄር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ የሚለው ስለዚህ ነው ፡፡
እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡5-6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #መገዛት #ሽማግሌ #ባለስልጣን #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment