እግዚአብሄር ሰውን ለክብሩ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር በሰው ላይ ይፈርዳል፡፡ እግዚአብሄር እውነተኛ ዳኛ ነው፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጠረው እንዲያደርግለት የሚፈልገውን ነገር ነግሮት ነበር፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገውን ነገር ሰው ካላደረገ እግዚአብሄር እንደሚቀጣው ነግሮት ነበር፡፡ እግዚአብሄር የሰዎችን አካሄድ በሚገባ በትጋት ይከታተላል ያስተካክላል፡፡
እግዚአብሄር ሁለት አይነት ሰዎችን ይቀጣል፡፡
የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤ ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። የሉቃስ ወንጌል 12፡47-48
የጌታውን ፈቃድ አውቆ ያላደረገ ሰው
ሰው የተፈጠረው እንዲታዘዝ ነው፡፡ እግዚአብሄር አመፀኛን ሰው ይቀጣል፡፡ እግዚአብሄር የማይታዘዝን ሰው ይቀጣል፡፡ አለመታዘዝ አመፅ ነው፡፡ የጌታን ፈቃድ ያወቀ ሰወ ፈቃዱን ማድረግ እንጂ ሌላ ምንም አማራጭ የለውም፡፡ የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፡፡
የጌታውን ፈቃድ ማወቅ ሲገባው ያላወቀ
የጌታን ፈቃድ ያላወቀ ሰው ሊቀጣ ይችላል፡፡ የጌታን ፈቃድ ያላወቀ ሰው ሁሉ ግን አይቀጣም፡፡ የጌታን ፈቃድ ያላወቀ ሰው ላይቀጣ ይችላል፡፡ የጌታ ፈቃድን ያላወቀ ሰው መቀጣቱና አለመቀጣቱ የሚወሰነው በደረጃው ነው፡፡ ሰው ባልደረሰበት ደረጃ አይቀጣም፡፡ ነገር ግን ከጊዜው የተነሳ እዚያ ደረጃ ላይ ባለመድረሱ በዚያ ይቀጣል፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል፡፡
ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ወደ ዕብራውያን 5፡12
አንድ ሰው ማድረግ ሲገባው በህይወቱ የሚያሳድጉትን ነገሮች ባለማድረጉ በስንፍናው ይቀጣል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የጌታፈቃድ #ይቀጣል #በብዙ #በጥቂት ##ታማኝ #ትጉህ #መክሊት #ትውልድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ሃሳብ #ገንዘብ #ጊዜ #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment