Popular Posts

Sunday, September 2, 2018

የእምነትና የተስፋ ልዩነቶች ክፍል አንድ


እምነትና ተስፋ ሁለት የተለያዩ ነገር መሆናቸውን መረዳት ተስፋ ብቻ ሲኖርን እምነት እንዳለን እንዳይመስለን ያስተምረናል፡፡ ተስፋና እምነት በክርስትያን ህይወት ውስጥ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡ ነገር ግን ተስፋና እምነት በፍጹም አንድ አይደሉም፡፡ ብዙ ሰዎች ግን የእምነትና የተስፋን ልዩነት በሚገባ ስለማይረዱ ተስፋና እምነት የሚሉትን ቃሎች በማቀያየር ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል፡፡
ተስፋ አንድ የሆነ ነገር እንዲሆን የመፈለግና የመጠበቅ ስሜት ነው፡፡
ተስፋ አንድ ነገር እንዲደርስ ወይም እውነት እንዲሆን መፈለግና መመኘት ነው፡፡
እምነትና ተስፋ የተለያዩ መሆናቸውን መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ተስፋ የማይታይን ነገር ይኖራል ብሎ መጠበባበቅ ነው፡፡
እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1313
እምነት ደግሞ አንድ ነገር እውነት ነው ብሎ መቀበል ነው፡፡
እምነት የማይታየውን አለም ማየት ነው፡፡ እምነት በማይታየው በመንፈሳዊ አለም ያለውን ማየትና ማወቅ ነው፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 417-18
ተስፋና እምነት የሚለያዩት ተስፋ የወደፊት ሲሆን እምነት የአሁን ነው፡፡
እምነት አሁን ነው፡፡ እምነት አሁን ካልሆነ መቼም አይሆንም ይላል፡፡ ተስፋ ግን ወደፊት ሊሆ ይችላል ይላል፡፡
እምነት አሁን በመንፈሳዊ አለም የሚሰማውን መስማት ነው፡፡ እምነት አሁን በመንፈሳዊ አለም የሚታየውን ማየት ነው፡፡ እምነት አሁን በመንፈሳዊ አለም የሚያዘውን መያዝ ነው፡፡ ተስፋ ደግሞ መጠበቅ ነው፡፡ ተስፋ ደግሞ መመኘት ነው፡፡ ተስፋ ደግሞ መፈለግ ነው፡፡
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ወደ ዕብራውያን 11፡1
እምነት ተስፋ ነው አይልም፡፡ እምነት የተስፋ የሚቀጥለው ደረጃ ነው፡፡ ተስፋ እምነት እንዲሆን የሚያስፈልገው ነገር አለ፡፡ እምነት የተስፋ ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት የተስፋ ማስረጃ ነው፡፡
ተስፋ አስፈላጊ ቢሆንም ተስፋ ብቻ ካለን ከእግዚአብሄር ልንቀበል አንችልም፡፡ በተስፋችን ላይ እምነት ካልተጨመረ ወደ ውጤት አይመጣም፡፡ ተስፋን ወደ ውጤት የሚያመጣው እምነት ነው፡፡
የመጀመሪያው ደረጃ በእግዚአብሄር ቃል ተስፋ ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ደረጃ ተስፋ ያደረግነውን ነገር በእምነት መያዝ ነው፡፡ 
እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር በእጃችን የሚያስገባ ነው፡፡ እምነት ተስፋ የምናደርግውን ነገር በመንፈስ እጃችን እንድንይዘው የሚያደርግ ነው፡፡
በእምነት አይን ነገሩ ሆኖዋል ተፈጽሟል፡፡ በተስፋ አይን ነገሩ ሊሆን ሊፈፀም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ፈውስን በተመለከተ ተስፋ ልፈወስ እችላለሁ ይላል፡፡ እምነት ግን ተፈውሻለሁ ብሎ እንደተፈወሰ ሰው ይኖራል፡፡
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡24
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment