Popular Posts

Follow by Email

Sunday, January 7, 2018

የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15
በምድር ብዙ ድምፅና ማስፈራራት አለ፡፡ አለም አይሆንም አትችልም አይሳካልህም በሚሉ ድምፆች የተሞላች ነች፡፡
አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም ጎሽ ቀጥሉ የእግዚአብሄርን ስራ እየሰራችሁ ነው፡፡ በትክክለኛ መንገድ ላይ ናችሁ ሰላም ነው እንድትለን መጠበቅ የለብንም፡፡ አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም በእኛ ላየ ነው የሚሰራው አንጂ ለእኛ አይደለም የሚሰራው፡፡ ከአለም እንደዚህ አይነትን ማረጋገጫ መጠበቅ ሃዘን ውስጥ ይከታል፡፡
ትክክልኛውንና እውነተኛውን ነገር የምንረዳው ከመንፈሳዊው አለም ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር የምናውቀው በመንፈሳዊው አለም ብቻ ነው፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
የእግዚአብሄርን ነገር የምንሰማው በልፀባችን ነው፡፡ ከግርግሩ ወጣ ብለን ወደልባችን መልስ ብለንብ ልባችንን የምንሰማበት ጊዜ ሊኖረን ይገባል፡፡ በዚህ መድር ላይ ትክክለኛውን ማረጋገጫ ሎሰጠን የሚችል ብቸኛው ነገር ልባቸነ ነው፡፡
አካባቢያችን በታላቅ ረብሻ ቢሞላም እንኳን ልባችን ሰላም ነው ካለ ሰላም ነው፡፡ አእምሮዋችን በጭንቀት ሃሳብ ቢወጠር እንኳን ልባችን ሰላም ከሆነ ሰላም ነው፡፡
ልባችን ሰላም ከሆነ ሁሉ ሰላም ስለሆነ እርፍ ልንል ይገባናል፡፡ የሚመራን የአለም ጩኸትና ማስፈራራት ሳይሆን ሂዱ ቁሙ እያል የሚመራን የክርስቶስ ሰላም ይሁን፡፡
ስለዚህ ነው ዘማሪ ተከስተ ጌትነት
ውስጤ ስሰማው ሳደምጠው
ሁሉ ሰላም ሰላም ነው
ውጭውን አይቶ ልቤ እንዳይሰጋ
እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ
በማለት የዘመረው፡፡
በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 315
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አእምሮ #መንፈስ #ሰላም #ልብ #አይታወክ #አይፍራ #ጭንቀት #ቅባት #ይግዛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment