የእግዚአብሔርን
ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ዕብራውያን 10፡36
የምናየው
ነገር ሁሉ የመጣው ከማይታየው ነገር ነው፡፡ የምናየው ነገር ሁሉ የማይታየው አለም ውስጥ የነበረ ነው፡፡ እምነትም የማይታየው አለም
ውስጥ ያለውን ነገር አይቶ ወደሚታየው አለም እስኪመጣ መጠበቅ ነው፡፡
ዓለሞች
በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3
የእግዚአብሄ
ፈቃድ ከመንፈሳዊው አለም ወደሚታየው አለም ከመምጣቱ በፊት የእኛን እምነትና ትግስት ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ነው ስትፀልዩ እንደተቀበላችሁ
እመኑ ይሆንላችኋል የሚለው፡፡ የሚታየው አለም ላይ ከመሆኑ በፊት ማመን ይጠይቃል፡፡
ስለዚህ
እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ሉቃስ 11፡24
የእግዚአብሄር
ፈቃድ ከማይታየው አለም ወደሚታየው አለም እስኪመጣ መጽናት ይጠይቃል፡፡ የእምነትን እርምጃ ከተራመድን በኋላ ውጤት እስከምናገኝ
ድረስ መታገስ ወሳኝ ነው፡፡
በእምነት
ጉዞ በተፈጥሮአዊ አይን የሚታየውን ባለማየት በመንፈሳዊ አይን የሚታየውን ደግሞ በማየት እንደሚቀበሉት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡
የማይታየውን
እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17
እግዚአብሄር
ተናገረን የእግዚአብሄን ፈቃድ አገኘን ማለት አካባቢ ሁሉ ከዚያ ቃል ጋር ከመቀጽበት ይስማማል ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውን የአካባቢ
ሁኔታ ተቃራኒውን ሊናገር ይችላል፡፡ ስሜታችን ከእግዚአብሄር ፈቃድ ተቃራኒውን ሊያሰማን ይችላል፡፡
ነፍሴ
ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። መዝሙር 43፡5
እግዚአብሄር
የተናገረንና የምናልፍበት ነገር እጅግ ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ነው ሁኔታዎች እንዳያጠራጥሩን በልቡ ሳይጠራጠር ብሎ መፅሃፍ ቅዱስ
የሚያስተምረው፡፡ ስሜታችንን ከተከተልን እንጠራጠራለን፡፡ ሁኔታውን ካየን እንጠራጠራለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሰምቶ በውሃ ላይ
ይራመድ የጀመረው ጴጥሮስ መስመጥ የጀመረው የአካባቢውን ሁኔታ አይቶ ስለተቀበለው እና ስለፈራ ነው፡፡
ነገር
ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ማቴዎስ 14፡30
ሁኔታም
ሆነ ስሜታችን ሁለቱም ድንበራቸው የሚታየው አለም ብቻ ስለሆነና አቅማቸው ስለማይፈቅድ ስለእምነት እና ስለ እግዚአብሄር ፈቃድ ሊመሰክሩ
አይችሉም፡፡
እውነት
እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።
ማርቆስ 11፡23
የአካባቢያችን
ሁኔታዎችና ስሜታችን ስለእግዚአብሄር ፈቃድ ሊመሰክሩ ብቁ አይደሉም፡፡ የአካባቢያችን ሁኔታዎችና ስሜታችን የምንታገሳቸው እንጂ ስለእምነት
ነገር እውነተኛ ምስክሮች አይደሉም፡፡
ስለዚህ
ነው መፅሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና የሚለው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment