ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7
መፅሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ እንደሌለ አድርጋችሁ ኑሩ ብሎ አይመክረንም፡፡
መጽሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ በራሱ እንዲሄድ ተስፋ አድርጉ አይለንም፡፡
መጽሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ስሙን አታነሱት እርሱም ይተዋችኋል አላለንም፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ስለ ዲያቢሎስ ወደ እግዚአብሄር ፀልዩ አላለንም፡፡
ስለዲያቢሎስ ወደእግዚአብሄር መፀለይ ሙሴ ባህሪን መክፈያውን በትር በእጁ ይዞ ወደ እግዚአብሄር እንደጮኽው አይነት የተሳሳት ጩኸት ነው፡፡
ሰው በእግዚአብሄ ክብር ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው በስልጣን እንዲገዛ ተፈጥሮዋል፡፡
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍጥረት 2፡27-28
ሰው አታድርግ የተባለውን ያንኑ ነገር በማድረጉና እግዚአብሄር ላይ በማመፁ የተነሳ የነበረውን መንፈሳዊ ስልጣን ለሰይጣን አስረክቦ ነበር፡፡
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ከሰው ስልጣኑን በመውሰድ የዚህ አለም ገዢ የነበረውን ሰይጣንን ስልጣን ለመሻር ነው፡፡
እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ ዕብራውያን 2፡14-15
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የሰይጣንን ስልጣንን ገፎታል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሉቃስ 10፡19
ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ተልእኮ በፍፁም የለው፡፡ ሰይጣን የሰውን ህይወት ሊሰርቅ ሊታርድ ሊያጠፋ ይመጣል፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10
ሰይጣን የማይቃወመው ሰው ካገኘ ህይወቱን ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡ ሰይጣን ሲመጣ ስልጣኑን የሚያውቅ የሚነግረው ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ስልጣኑን ተረድቶ የሚቃወመው ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ከህይወታችን እና የእኛ ከሆኑት ነገሮች ለመሸሽ ትእዛዛችንን ይጠብቃል፡፡
ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #እባቡ #ጊንጥ #ሥልጣን #ተቃወሙ #ይሸሻል #ገፎ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment