የእግዚአብሔር
ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን
እንዲያመልክና እንዲያገለግል ነፃ ወጥቷል፡፡ ስኬት የተፈጠሩለትን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡ ስኬት ለተፈጠሩነት አላማ
መኖር ነው፡፡ ስኬት የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ደግሞ በህይወታችን
ፈቃዱን መለየት አለብን፡፡ በምድር ላይ ብዙ ድምፆች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእነዚያ ብዙ አይነት ድምፆች መካከል መለየት
ለእግዚአብሄርን ፈቃድ ኖረን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመለየት አእምሮዋችን በእግዚአብሄር
ቃል መታደስ አለበት፡፡ በአለም አስተሳሰብ በተበላሸ አእምሮ የእግዚአብሄን ፈቃድ መለየት በፍፁም አይቻልም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ
በሚገባ መለየት የሚችል እእምሮ በእግዚአብሄርን ቃል የታደሰ አእምሮ ብቻ ነው፡፡
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር
ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
አእምሮዋችን ከተሳሳተ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ
ካልሆነ አለማዊ አስተሳሰብ በእግዚአብሄር ካልታደሰና ካልተለወጠ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መለየት ይሳነናል፡፡
አእምሮዋችንን ከሌሎች አስተሳሰቦች ሊያፀዳና እንደ
እግዚአብሄር ቃል ሊለውጥና ሊያድስ የሚችለው የእግዚአብሄርን ቃል ማንበብና ማሰላለስ ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት
ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ጌታ #አእምሮ #ማደስ #መለወጥ
#መከተል #መከተል #መምሰል #እግዚአብሔርንመምሰል #ቃል
#ተማሪ #መንፈስቅዱስ
#ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ
#ተከታይ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment