ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኙ የተቀበለ ሰው ሁሉ
አዲስ ፍጥረት ነው፡፡ እንደ አዲስ ፍጥረት ለማፍራት ለእግዚአብሄር ነገር ግድ የሌለውን ስጋዊ ምኞትን እንቢ ማለት አለብን፡፡ ስጋ
ደግሞ የእግዚአብሄርን ነገር የማይፈልግ በመንፈሳዊው ወጭ ለጊዜው ብቻ መደሰት መዝናናት የሚፈልግ ነው፡፡
ስጋ እንዲበረታና እርሱን እንዲመራው የሚያደርገው
ሰው ነው፡፡ ሰው ስለስጋ በማሰብ ስጋዊ ምኞት እንዲያሸንፈው ያደርጋል፡፡ ነገር ግን በመንፈስ የሚመላለሱ ስጋን ከክፉ መሻቱ ጋር
ሰቀሉት እንደሰቀሉት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ገላትያ 5፡24
ሰው ቁጭ ብሎ ስለስጋ የሚያስብ ፣ የሚያወጣና
የሚያወርድ ከሆነ ለስጋ መጠንከርና ማሸነፍ ያመቻችለታል፡፡ ሰው ስጋውን ሰለማስደሰት ግድ የሚለውና ስጋውን ለማስደሰት የሚያስብና
የሚያቅድ ከሆነ ስጋ እየበረታ እያሸነፈ ይሄዳል፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥
መገዛትም ተስኖታል፤ ሮሜ 8፡5-7
ስጋ
እንዳይበረታና እንዳያሸንፍ የሚያደርገውም እንዲሁ ሰው ነው፡፡ ሰው ስጋን እንደጠላት በማየት ስለስጋ ባለማሰብ ስጋ እንዳያሸንፍ
ማድረግ ይችላል፡፡ ሰው ስለስጋ ባለማሰብ ብቻ ስጋ ምኞቱን እንዳይፈፅም እንቅፋት ሊሆንበት ይችላል፡፡ ሰው ስለስጋ ባለማሰብ በስጋ
ላይ መንገድን ሁሉ ሊዘጋበት ይችላል፡፡
ሌሊቱ
አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፡12-14
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ስጋ #ምኞት #ማሰብ #ህይወት #ሞት #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና
No comments:
Post a Comment