Popular Posts

Tuesday, January 23, 2018

የእውነተኛ ባለጠጋ አስራ ሶስት ምልክቶች

ብዙ ባለጠጋ ያልሆነ ሰው ባለጠጋ እንደሆነ ለመምሰል ይጥራል፡፡ እውነተኛን ባለጠጋ የምንለየው በአስተሳሰቡ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በአስተሳሰቡ የበለጠገ ነው፡፡
1.      እውነተኛ ባለጠጋ ማንም ባለጠጋ መሆን እንደሚችል ያምናል፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ እርሱ ባለጠጋ የሆነው እርሱ ብቻውን ሱፐር ስታር ስለሆነ እንደሆነ አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠጋ የሆነው እርሱ ብቻውን የተመረቀ ስለሆነ አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ማንም እግዚአብሄር ጊዜውን ያመጣለት ሰው ባለጠጋ ሊሆን እንደሚችል ያምናል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ሲያድግ አብረውት ማደግ ያለባቸው ሰዎች እንዳሉ ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ እድገቱን በራሱ ላይ ብቻ አያውለውም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ አብሮ በማደግ ሌሎችን በማንሳት ያምናል፡፡
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11
2.     እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን አይፈራም፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን ያውቀዋል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የድህነትን ውስንነት ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን አይፈራም ባለጠግነትን አያከብርም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነት እንዳይመጣባቸው ማናቸውንም የተሳሳተ ነገር እንደሚያደርጉት ሰዎች ድህነትን አይሰግድለትም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የድህነትንም የብልጥግናንም ልካቸውን ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትም ሃብት ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚያኖር ያውቃል፡፡
መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12-13
3.       ባለጠጋ የሆነ ሰው ባለጠጋ ለመምሰልና ባለጠግነቱን ለማሳየት አይጥርም፡፡
ባለጠጋ የሆነ ሰው አላማውን ይኖራል፡፡ ባለጠጋ የሆነ ሰው ከማንም ጋር አይፎካከርም፡፡ ባለጠጋ የሆነ ሰው ማንንም ለመብለጥ አይጥርም፡፡ ባለጠጋ ጎረቤቱን ተንጠራርቶ ሳያይ በቤቱ የሚያስፈልገውን ብቻ ያደርጋል፡፡
ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤
እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና። ገላትያ 6፡4-5
4.       ባለጠጋ የሆነ ሰው ማንም ሰው ባለጠጋ ሊሆን እንደሚችል ያምናል
እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት የውስጥ እንደሆነ ያምናል፡፡ እውነተዓ ባለጠጋ ባለጠግነቱ ብርጭቆ ከእጅ ወድቆ እንደሚሰበር አጣለሁ ብሎ አይፈራም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በድንገት ባለጠግነቱን እንደሚያጣው አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት በገንዘብ ውስጥ በእውቀት ውስጥና በሃይል ውስጥ ሳይሆን እውነተኛ ባለጠግነት በሰው ውስጥ እንዳለ ያምናል፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት መንፈሳዊ ስሌት እንደሆነ ያስባል፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት ከምድራዊ አካውንት ጋር የማይጨምርና የማይቀንስ ልዩ መንፈሳዊ አካውንት እንደሆነ ያውቃል፡፡
በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ፊልጵስዩስ 4፡17
5.       እውነተኛ ባለጠጋ በመልካም ስራ ባለጠግነቱ ይታወቃል፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ መታወቅ የሚፈልገው ባለው ገንዘብ ሳይሆን ባለው ገንዘብ ተጠቅሞ በሰራው መልካም ስራ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት በመልካም ስራ እንጂ በገንዘብ እንዳይደለ ያውቃል፡፡
እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19
6.       እውነተኛ ባለጠጋ በምህረትም በይቅርታም የበለጠገ ነው፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነቱ ግንጥል ጌጥ ያለሆነ በሁሉም የህይወት ዘርፉ ያደገ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በነፍሱ የበለጠገ ነው፡፡ 
ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። 3 ዮሐንስ 1፡2
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ኤፌሶን 2፡4
7.       እውነተኛ ባለጠጋ ልቡ ሰፊ ነው
እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘብ እንደሚመጣና እንደሚሄድ የሚረዳ ከምንም በላይ ለሰው ልጅ አክብሮት ያለው ልቡ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ቋጣሪ አይደለም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የእሱ በረከት ከሰው ጋር እንደማይገናኝና የገንዘቡን ንጥቂያ በፀጋ የሚቀበል ነው፡፡
የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እብራዊያን 10፡34
8.       እውነተኛ ባለጠጋ በቅንጦት ላይ ገንዘቡን ላለማጥፋት ይጠነቀቃል፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ ያለው ገንዘብ መሰረታዊ ፍላጎት ማሟያ እንደሆነ የቀረው ግን የሚያካፍለውና የሚሰጠው እንደሆነ ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በቅንጦት ላይ ገንዘቡን ላለማባከን የለመደ በልክ የሚኖር ሰው ነው፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1 ጢሞቴዎስ 6:6-8
9.       እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘቡን እጅግ አስተማማኝ ቦታ ላይ የሚያከማችና እጅግ አትራፊ ነፍስን የሚያድንበት ቦታ ላይ የሚዘራ ነው፡፡
ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ማቴዎስ 6፡19-21
እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9
10.    እውነተኛ ባለጠጋ በህይወት እጅግ አስፈላጊ ነገሮች ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችሉ በነፃ የሚሰጡ ስጦታዎች እንደሆኑ ያስባል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘብ እጅግ ውስን እንደሆነና ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው እጅግ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ያውቃል፡፡
እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡4
11.     እውነተኛ ባለጠጋ ኑሮውን እየኖረ እየተደሰተ እንጂ ባለጠጋ ለመሆን ህይወትን አያቆምም ደስታውንም ለወደፊት አያስተላልፍም፡፡  
እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት የህይወትን ስጦታ አያጎሳቁልም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ወዳጁም አያጣም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ደስታውን አያጣም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ሰላሙን የሚያሳጣ ነገር አያደርግም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት የሰውን በጎ ፈቃድ የሚያሳጣውን ነገር አያደርግም፡፡  
እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡18-19
12.    እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት አይቸኩልም፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት በጊዜ ውስጥ በሚፈታን ታማኝነት የሚገኝ እንጂ በአንዴ የማይገኝ እንደሆነ ያውቃል፡፡
የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11
13.    እውነተኛ ባለጠጋ ስለሃብቱ አይመካም፡፡
እውነተኛ ባለጠጋ ስለሃብቱ እግዚአብሄርን ብቻ ያመሰግናል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 9፡23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

No comments:

Post a Comment