Popular Posts

Monday, January 22, 2018

ሞትን የሚፈራ ሰው ህይወትን አያይም

የሞት ፍርሃት እስራት ነው፡፡ ሰው ከሞት ፍርሃት ነፃ ካልሆነ ለመኖር ነፃ አይሆንም፡፡ የሞት ፍርሃት ጭቆና ነው፡፡ የሞት ፍርሃት ክፉ እስራት ነው፡፡ ሰው የሞት ፍርሃት እያለበት በነፃነት መኖር አይችልም፡፡ ሞትን የሚፈራ ሰው እንደሚገባው መኖር ያቅተዋል፡፡
በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብራውያን 2፡14-15
ሰው በሞት መገኘት ከደነገጠ በህይወት ስኬታማ መሆን አይችልም፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። መዝሙር 23፡4
ከሞት ፍርሃት ነፃ የወጣ ሰው በሞት መገኘት ነፃ ሆኖ ይመላለሳል፡፡ ከሞት ፍርሃት ነፃ የሆነ ሰው ከሞት ፍርሃት በላይ የእግዚአብሄር እረኝነት ይሰማዋል፡፡ ከሞት ፍርሃት ነፃ ለወጣ ሰው ሞት ጥቅም ነው፡፡ ባለው ዘላለማዊ ህይወት የሚተማመን ሰው በስጋ መለየት የተሻለ ነው፡፡  
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ፊልጵስዩስ 1፡21
ለእግዚአብሄር አላማ ለሚኖር ሰው ሞት ከሸክምና ከሃላፊነት መገላገል ነው፡፡ ለእግዚአብሄር አላማ ለሚኖር ሰው ሞት ከምድር ሃላፊነት መመረቅ ነው፡፡
በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡6-8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ሃይል #ዘላለም #ህይወት #ሞት #ፍርሃት #ጥቅም #መለየት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዘላለማዊነት  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment