እምነት በተፈጥሮአዊው አለም የማይታየውን ማየት
ነው፡፡ እምነት መንፈሳዊውን አለም ማየት መቻል ነው፡፡ እምነት ልእለ-ተፈጥሮአዊውን አለም ማየት ነው፡፡
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1
እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር የሚያስረግጥ
ነገር ነው፡፡ እምነት የተስፋ ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት ተስፋችን እንደሚፈጸም ማረጋጫ ነው፡፡
እምነት ተስፋ ማድረግ ብቻ አይደለም፡፡ እምነት
ተስፋ የምናደርገውን ነገር ማስረጃ ነው፡፡ እምነት ተስፋችን እንደሚፈፀም ማረጋገጫው ነው፡፡
እምነትና ተስፋ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ እውነት
ነው ለእምነት ተስፋ ያስፈልጋል፡፡ ተስፋ ብቻ ግን አምነት አይደለም፡፡ ተስፋ እና የተስፋ ማረጋገጫው በአንድነት እምነት ይባላል፡፡
ተስፋ አንድ ነገር ወደፊት እንደሚሆን መጠበቅ
ነው፡፡
በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ሮሜ 8፡24-25
ተስፋ አስፈላጊ ነው፡፡ ካለ ተስፋ እምነት አይኖርም፡፡
ተስፋ አለን ማለት ግን እምነት አለን ማለት አይደለም፡፡ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ይላል፡፡
. . . በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24
አንድ
ሰው ወደፊት እንደሚፈወስ ተስፋ አለኝ ካለ ተስፋ አለው ማለት ብቻ ነው፡፡ ተስፋ ብቻ ለመፈወስ አይበቃም፡፡ ተስፋና የተስፋው ማረጋገጫ
የሆነው እምነት ሲኖረን እንፈውሳለን፡፡ ለመፈወስ ተስፋ ብቻ ሳይሆን እምነት ይጠይቃል፡፡
ሰው
እምነት ሲኖረው ይፈወሳል፡፡ ሰው ግን በተስፋ ብቻ አይፈወስም፡፡ ተስፋው ማረጋገጫ ካለው ይፈወሳል፡፡ ተስፋ ማረጋገጫው እምነት
ከሌለው አይፈውስም፡፡
ሰው
እግዚአብሄር በኢየሱስ የሰራለትን ለፈውሱ የተከፈለለትን ክፍያ ከእግዚአብሄር ቃል ሲረዳ ይፈወሳል፡፡ ሰው በኢየሱስ መገረፍ ቁስል
እንደተፈወሰ ሲያምን ተስፋ አያደርግም፡፡ ሰው በኢየሱስ መገረፍ ቁስል እንደተፈወሰ ሲያምን እምነቱን ይቀበላል፡፡
ሰው
እንደተፈወሰ ሲያምን ተስፋ ማድረጉን ያቆማል፡፡ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ይላል መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ የሚያየውን ተስፋ የሚያደርግ
ሰው የለም፡፡ የሚያየውን ያመሰግንበታል ይጠቀምበታል እንጂ የሚያየውን ማንም ተስፋ አያደርገውም፡፡
እንደዚሁ
በመገረፉ ቁስል እንደተፈወሰ ያመነ ሰው ተስፋ አያደርግም፡፡ ምክኒያቱ ተስፋ ሊመጣም ላይመጣም ይችላል፡፡ በመገረፉ ቁስል የተፈወሰ
ሰው እግዚአብሄርን ስለፈውሱ ያመሰግናል እንደተፈወሰ ሰው ይኖራል፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment