Popular Posts

Monday, May 1, 2017

ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 310
የምድር ችግር ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ የሰይጣን ማጥቂያውም መንገድ ብዙ ነው፡፡ ስለዚህ ዘርፈ ብዙ ለሆነ ችግር ቀላል መልስ የለውም፡፡ ዘርፈ ብዙ ለሆነ የጠላት ጥቃት አንድ መከላከያ የለውም፡፡
ጠላትን ባለን ነገር ሁሉ ነው የምንቋቋመው፡፡ 
እግዚአብሄርም ለጠላት ዘርፈ ብዙ ማታለል መድሃኒት የሆነውን ዘርፈ ብዙ ጥበብ ሰጥቶናል፡፡
በብሉይ ኪዳንም እንዲህ ተብሎ ተፅፏል፡፡  
ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ። ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል። 1ኛ ነገሥት 19፡17
ጠላትን ድል የምንነሳው በአምልኮም ነው ፣ በእምነት እወጃም ነው ፣ በፀሎትም ነው ፣ በትእግስትም ነው ፣ በትጋትም ነው ፣ በመጠበቅም ነው ፣ በፀጥታም ነው ፣ በአንድነትም ነው ፣ በምስጋናም ነው ፣ በመንፈስ በመመራትም ነው ፣ በመስጠትም ነው ፣ በጥበብም ነው ፣ በይቅርታም ነው፡፡
ስለዚህ ነው አውቃለሁ ማለት የሌለብን ፣ ስለዚህ ነው በቀጣይነት የእግዚአብሄን ጥበብ ከእግዚአብሄር ቃል ውስጥ መፈለግ ያለብን ፣ ስለዚህ ነው በቀጣይነት የእግዚአብሄን ፊት መፈለግ ያለብን፡፡
ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 3፡10
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment