Popular Posts

Tuesday, May 30, 2017

እግዚአብሄር ልብን አይቶ ያደላል

እግዚአብሄር የሰውን ፊትን አይቶ አያዳላም፡፡ የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት እግዚአብሄር ሰውን በውጫዊ ነገር በአነጋገሩንና በአለባበሱ አይመዝንም ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ንጉስን ሊመርጥ ሲል ለንጉስነት የሚቀባው ነቢይ የሰውን ፊት ያይ ስለነበረ ቁመታቸው ዘለግ ያለውን ሰዎች ለንጉስንት ሊቀባ ነበር፡፡
እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 16፡6-7
እግዚአብሄር ሰው እንደሚያይ አያይም ፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ በውጭ በሚያየው ውስን ይሆናል፡፡ ሰው ማየት የሚችለው ፊትን ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችልው የውጫዊውን ገፅታ ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችለው የሰውን ልብስ እና የሚነዳውን መኪና ነው፡፡ ሰው ሰውን የሚመዝነው በውጫዊ ማየት በሚችልው በውጫዊ ነገር ብቻ ነው፡፡
ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ። ሐዋርያት 10፡34-35
ሰው እንደሚያይ እግዚአብሄር አያይም፡፡ እግዚአብሄር የሰው መመዘኛ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ከልብስና ከውጫዊ ገፅታ ባሻገር የሰውን ዋናውን ነገር ልብን ማየት ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰው ያከበረውን እግዚአብሄር ሊንቀው ይችላል፡፡ ሰው የናቀውን ደግሞ እግዚአብሄር ሊያከብረው ይችላል፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና። ሮሜ 2፡11
እውነት ነው እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ ይህ ማለት ግን እግዚአብሄር አይመዝንም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት ግን እግዚአብሄር መመዘኛ የለውም ማለት አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የራሱ መመዘኛ አለው፡፡ የእግዚአብሄር መመዘኛ እንደ ሰው መመዘኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፊትን እይቶ አያዳላም እንጂ እግዚአብሄር ግን የራሱ ምርጫ አለው፡፡ እግዚአብሄር ይመርጣል፡፡ እግዚአብሄር የሚመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር የማይመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው ስው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የማያስደስተው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያዘነብላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው አያዘነብልም፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያደላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው ደግሞ አያደላም፡፡ እግዚአብሄር ግን ያደላል፡፡
እግዚአብሄር ፊትን አይቶ አያዳላም እንጂ ልብን አይቶ ግን ያደላል፡፡ እግዚአብሄር የሰው ልብ ይማርከዋል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ልብ ይመዝናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የልብ አይነት አለ፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
እግዚአብሄር ልብን አይቶ ማድላት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፍፁም ልብ ባለው ሰው ህይወት ሃይሉን ለመግለጥ ፈልጎ አይኖቹ በምድር ላይ ይመላለሳሉ፡፡  
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። 2ኛ ዜና 16፡9
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሚለው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 3፡5፣ 4፡23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ልብ #ዋጋ # #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment