ፍቅር
ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4
ቅናት
ከሌላው ሰው አንፃር ከደረጃ መውረድን ወይም መክሰርን ከመፍራት የሚመጣ ስጋት እና የመረበሽ ስሜት ነው፡፡
ቅናት
ሌሎች ይበልጡኛል ፣ ጥለውኝ ይሄዳሉ እወድቃለሁ ከሚል ስጋት ይመነጫል፡፡
ቅናት
የሚመጣው ራስን ካለማወቅ ነው፡፡ ቅናት የሚመጣው ከሌላው ጋር ከመፎካከር ነው፡፡ ቅናት የሚመጣው
የራስን ዋጋ ካለማወቅ ነው፡፡ ቅናት የሚመጣው የራስን አስፈላጊነት ካለመገንዘብ ነው፡፡ ቅናት የሚመጣው ምንጭን ካለመረዳት ነው፡፡
እግዚአብሄርን ምንጩ ያደረገ ሰው አይፈራም፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
የተለየ ጥሪ እንደለውና እግዚአብሄር የወሰነለት የተለየ ስጦታ እንዳለው የሚያውቅ
ሰው አይፎካከርም አይቀናም፡፡
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ
አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። እኛ
ግን እግዚአብሔር እንደ ወሰነልን እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ ያለ ልክ አንመካም። 2ኛ ቆሮንቶስ
10፡12-13
ፍቅር ሰዎች የሚያድጉት በእርሱ ወጭ እንደሆነ አያስብም፡፡ ፍቅር የራሱ ድርሻ እንዳለውና
የእርሱን ድርሻ ሊወስድ የሚችል ሌላ ሰው እንደሌለ በእግዚአብሄር ይተማመናል፡፡
ፍቅር ሌላው ሲያገኝና ሲሳካለት እርሱ እንደተሳካለት ደስ ይለዋል፡፡ ፍቅር የሌላው
ስኬት የስኬቱን ባለቤት እግዚአብሄርን ስለሚያሳየው በሌላው ስኬት ሃሴት ያደርጋል፡፡
የሚቀና ሰው ግን ከራሱ ስኬት በላይ የሌላው ውድቀት ያስደስተዋል፡፡
ፍቅር እግዚአብሄር ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ እንደሆነና የእግዚአብሄር በረከት ለሁሉም
እንደሚበቃ ያምናል፡፡ ፍቅር እርሱ እንዲሳካለት ሌላው መሰናከል እንደሌለበት ይረዳል፡፡ ፍቅር ሌላው የተሳካለት ደግሞ በእርሱ መሰናከል
እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ ፍቅር የእርሱ ሻማ እንዲበራ የሌላው ሻማ መጥፋት እንደሌለበት ይረዳል፡፡
ፍቅር አይቀናም፤
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #ቅናት #ስጋት #ፍርሃት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment