Popular Posts

Saturday, May 13, 2017

ፍቅር - የትእዛዝ ኢላማ

የእግዚአብሄር ትእዛዝ ብዙና ውስብስብ ቢመስልም ግን ከባድ ያልሆነና በአንድ ቃል ሊጠቃለል የሚችል ትእዛዝ ነው፡፡
የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1 ጢሞቴዎስ 15
በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የምትመለከቷቸው ማናቸውም ትእዛዞች አላማቸው በፍቅር እንድንኖር ማስቻል ነው፡፡ እያንዳንዱ ትእዛዝ በፍቅር ኑሩ የሚለው ትእዛዝ ትንታኔና ማብራሪያ ነው እንጂ አዲስ ትእዛዝ አይደለም፡፡
ማንኛውም ትእዛዝ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋርና ከሰው ጋር በፍቅር እንዲኖሩ ካላበረታታ አላማውን ስቷል፡፡ በፍቅር የመኖር ግብ የሌለውን ትእዛዝ ያለመቀበል ሙሉ መብት አለን፡፡ ትእዛዛት የተሰጡት እኛ በፍቅር እንድንኖር ለማስቻል ነው፡፡
የእግዚአብሄር ትእዛዛት ሁሉ ሲጨመቁ እግዚአብሄርን ውደድ ባልንጀራህን ውደድ በሚል ትእዛዝ ይጠቃለላሉ፡፡
እርሱም በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው? እንዴትስ ታነባለህ? አለው። እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። ሉቃስ 1026-27
በፍቅር የሚኖር ሰው ከመቀፅበት ትእዛዛትን ሁሉ ይፈፅማል፡፡ በፍቅር የማይኖር ሰው ደግሞ ትእዛዛትን ሁሉ ይተላለፋል፡፡
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ሮሜ 138
የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1 ጢሞቴዎስ 15
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #በፍፁምልብ #በፍፁምሃሳብ #በፍፁምነፍስ #በፍፁምሃይል #መውደድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment