በምድር ላይ ተቋቁሞ ለማለፍ እንዲሁም ከማንኛውንም
ክፋት ለመዳን እግዚአብሄርን መፍራት በጣም ወሳኝ ነው፡፡
እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ደግሞ እግዚአብሄርን
እንደ እግዚአብሄርነቱ መጠን ማክበር እና መስማት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ለእግዚአብሄር ፈጣሪነትና አምላክነት
እውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር መፍራት ማለት እኛ የእግዚአብሄር ፍጥረት እንደሆንን ለራሱ ለክብሩም እንደፈጠረን መረዳት
ማለት ነው፡፡
እግዚአብሄርን አለመፍራት ማለት ደግሞ በሃሳባችን
፣ በንግግራችንና በድርጊታችን ለእርሱ ፈቃድ ቦታ አለመስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን አለመፍራት ማለት በህይወታችን ለእርሱ
ሀሳብ ቅድሚያ አለመስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን አለመፍራት
ማለት ፍላጎቱን ከቁጥር አለማስገባት ማለት ነው፡፡
ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ
መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ሮሜ 1፡20-21
ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ስለተፈጠረ እግዚአብሄርን
እንደ እግዚአብሄርነቱ ካላከበረው ህይወቱ ይወሳሰባል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካልፈራ ምንም ነገሩ ሊቃና አይችልም፡፡
ሰው እግዚአብሄርን ከፈራ ደግሞ በህይወቱ ሁሉም
ነገሩ መስራትና መሳካት ይችላል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ከፈራ ሌላ ሁሉ ነገሩ ትክክለኛ ቦታውን ይይዛል፡፡
1.
እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ጥበበኛ ነው፡፡ እግዚአብሄርን
የሚፈራ ሰው ለህይወቱ ያውቅበታል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ከሰማይና ከምድር ፈጣሪ ጋር እንዴት እንደሚኖር የሚያውቅ አስተዋይ
ነው፡፡
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ምሳሌ 1፡7
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል። መዝሙር 111፡10
2.
እግዚአብሄርን የምትፈራ ሴት የተመሰገነች ነች፡፡ እግዚአብሄርን
የሚፈራ ሰው የሚደነቅ ሰው ነው፡፡
ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ምሳሌ 31፡30
3.
እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው መልካም ከሚባል ምንም ነገር
አይጎድልም፡፡
የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት። መዝሙር 34፡9
4.
እግዚአብሄር የሚፈሩትን ፀሎታቸውን ይሰማል ምኞታቸውንም ያደርጋል፡፡
ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም። መዝሙር 145፡19
5.
የሚፈሩት ሰዎች ይበልጥ ረጅም
እድሜ እንዲኖሩ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፤ የኀጥኣን ዕድሜ ግን ታጥራለች። ምሳሌ
10፡27
6.
እግዚአብሄርን መፍራት ገንዘብና ንብረት ከማያስጥለንን
አደጋ ያስጥለናል፡፡
ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው። ምሳሌ 14፥27
7.
የሚፈሩ ሰዎች እግዚአብሄርን
ያስደስቱታል፡፡
እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል። መዝሙር 147፡11
8.
እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሰዎች እግዚአብሄር በመላክቱ ይጠብቃቸዋል
ያድናቸውማል፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። መዝሙር 34፡7
9.
እግዚአብሄር በሚፈሩትን ሰዎች ፋንታ ሃይሉን ይገልፃል፡፡ ራሱን እና ቃልኪዳኑን ይገልጥላቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። መዝሙር 25፡14
10.
እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ከራሱ አልፎ ለትውልዱ ጠንካራ
መታመኛን ያዘጋጃል፡፡
እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል። ምሳሌ 14፡26
11.
ልጅ ለአባቱ እንደሚራራ እግዚአብሄር ለሚፈሩት ይራራል፡፡
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ መዝሙር 103፡13
12.
እግዚአብሄርን ፈርቶ የሚስት
ሰው የለም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በመፍራቱ ወደ ህይወት ይመራል፡፡
እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም። ምሳሌ 19፥23
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት
#ሃሳብ #ጥበብ
#ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት
#ጥበብ #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ
#እምነት #ቃል #ማደስ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment