ደቀመዛሙርቱ በስጋ ውስጥ የማይኖር መንፈስ ብቻ ያዩ ስለመሰላቸው ኢየሱስ ስጋ እንዳለውና በስጋ ውስጥ እንደሚኖር አሳያቸው፡፡ ሰው ነፍስ የሌለው በስጋ ውስጥ የማይኖር መንፈስ ብቻ አይደለም፡፡
እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። ሉቃስ 24፡39-40
ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረ ፍጥረት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚመስለው በነፍሱና በስጋው አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የሚመስለው መንፈሱ ነው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ . . . እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ ዘፍጥረት 1፡26-27
እግዚአብሄር ነፍስ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ስጋ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሃንስ 4፡24
እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳለ ከፈጠረውና እግዚአብሄር ደግሞ መንፈስ ከሆነ ሰው ነፍስ ወይም ስጋ ሊሆን አይችልም፡፡
ሰው ነፍስ ማለትም ስሜት ፣ ሃሳብ እና ፈቃድ ያለውና በስጋ ውስጥ የሚኖር ፍጥረት ነው፡፡
ሰው ሲፈጠር እግዚአብሄር የሰውን ስጋ ከምድር አፈር አበጀው፡፡ እግዚአብሄር የሰወን መኖሪያ ስጋውን ከሰራው በሁዋላ ሰውን በመኖሪያው ስጋ ውስጥ ፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር የህይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፡፡ እግዚአብሄር በስጋ ውስጥ ስለማይኖር ኦክስጅን አይተንፍስም፡፡ የእግዚአብሄር የህይወት እስትንፋሱ መንፈስ ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። ዘፍጥረት 2፡7
ሰውም ሲሞት የሞተው መንፈሱ ነው፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒያት ሲሞት ስጋውና ነፍሱ ወዲያው አልሞተም፡፡ ሰው አትብላ የተባለውን በበላ ቀን የሞተው መንፈሱ ነው፡፡
ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡17
ስለስጋውና ስለነፍሱ የሚናገረው መዝሙረኛው ዳዊት ስጋ ወይም ነፍስ እንዳይደለ እንረዳለን፡፡
ጠላቶቼ ሁልጊዜ፦ አምላክህ ወዴት ነው? ባሉኝ ጊዜ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ። ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። መዝሙር 42፡10-11
ኢየሱስ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ የሚለው ነፍሱን ወይም ደግሞ ስጋውን አይደለም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3
ከመንፈስም የሚወለደው ነፍሱ ወይም ስጋው አይደለም፡፡ ከመንፈስ የሚወለደው መንፈሱ ነው፡፡
ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዮሐንስ 3፡5-6
በስጋ ስኖር ከስጋ ስለይ እያለ የሚናገረው ሐዋሪያው ጳውሎስ ነፍስ ወይም ስጋ አይደለም፡፡
በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ፊልጵስዩስ 1፡23-24
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መንፈስ #ነፍስ #መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ስጋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ዳግመኛመወለድ
No comments:
Post a Comment