ልጅ ወልደው በትጋትና የሚያሳድጉ እናቶች የተባረኩ ናቸው፡፡ ለወለዱት ልጆቻቸው የመስዋእትነት ፍቅርና እንክብካቤ የሚያደርጉት የተባረኩ እናቶች ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
ላልወለዱዋቸው ልጆች ተመሳሳይ እንክብካቤ የሚያደርጉ እናቶች ይበልጥ የተባረኩ ናቸው፡፡
አንዲት ሴት ቃለ መጠይቅ እየተደረገላት ነበር ፡፡ በቃለ መጠይቁ መካከል ልጆች አለሽ ወይ ተብላ ለተጠየቀችው ጥያቄ ልጆች አልወለድኩም ብላ መለሰች፡፡ ልጆች መውለድ አላስፈለገኝም ምክኒያቱም በአጠገቤ ተወልደው እንዴት እንደሚያድጉ የጨነቃቸው ብዙ ልጆች አሉ እነርሱን አሳድጋለሁ ብላ መለሰች፡፡ ንግግርዋ ልቤን ነካኝ፡፡ ይች እናት ልጆቻቸውን ወልደው እንክብካቤ ከማያደርጉ እናቶች ይበልጥ የተባረከች ናት፡፡
አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸው ልጆች ይወልዱና ተጨማሪ ልጆችን በማደጎ ያሳድጋሉ፡፡ ያልወለዱዋቸው ልጆች ከወለዱዋቸው ልጆች እኩል የእናትነት እንክብካቤ እንዲያገኙ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የእናትነት እንክብካቤ የጎደላቸውን ልጆችን በያሉበት ይንከባከባሉ፡፡
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው። ያዕቆብ 1፡27
ከወለዱዋቸው ልጆቻቸው አልፈል ለሌሎች የእናትነት እንክብካቤ የሚሰጡ እናቶች ይልቅ የተባረኩ ናቸው፡፡
መልካም የእናቶች ቀን!
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ #ቃል #ደግነት #ቸርነት #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment