እግዚአብሄርን
ማገልገል ከምንም ነገር በላይ የከበረ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እንዲያመልከውና እንዲያገለግለው ነው፡፡ እግዚአብሄር
የእስራእኤል ህዝብን ከግብፅ ሲያወጣ እንዲያገለግለኝ ህዝቤን ልቀቅ ነው ያለው፡፡
የተፈጠርንበትን
እንዲሁም በእግዚአብሄር የዳንንበትን ዋናውን አላማ እግዚአብሄርን የማገልገል ሃላፊነታችንን እንዳንፈፅም ህይወታችንን ከንቱ ሊያደርጉ
የሚመጡ የህይወት አንቅፋቶች አሉ፡፡
እግዚአብሄርን
የሚያገለግል ሰው የተፈጠረበትን አላማ ይፈፅማል እግዚአብሄርም እርሱን ያከብረዋል፡፡
የሚያገለግለኝ
ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል። ዮሐንስ 12፡26
ባለን
ነገር አለመርካት
ባለው
የሚረካ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የሚችለው፡፡ ሰው ባለው ነገር በረካበት መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የሚችለው፡፡
ኑሮዬ
ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8
ጌታን
እንደምናገለግል አለማወቅ
ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። ቆላስይስ
4፡17
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን
ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላስይስ 3፡23-24
የአለም
ሃሳብ
የህይወት
ሃላፊነቶቻችንን ለእግዚአብሄር ካልሰጠናቸውና እግዚአብሄር በሰጠን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን የመፈለግ ሃላፊነታችን ላይ
ካላተኮርን እግዚአብሄርን ማገልገል የሚባለው ነገር ዘበት ነው፡፡ ፊት ከሰጠነው የኑሮ ሃሳብ በቁማችን ሊውጠን የሚችል ብዙዎችን
ከአገልግሎት አስፈራርቶ ከንቱ ያደረገ ነገር ነው፡፡
የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19
ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33
ክርስቶስን
አለመመልከት
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
የእግዚአብሄርን
ፀጋ አለመረዳት
እግዚአብሄርን
የምናገለግለው በእርሱ በራሱ ወጭ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው በራሱ ሃይል እንደሆና ካላወቅን እንታክታለን፡፡
አብረንም
እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ
አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣3-4
ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት
ስላለን አንታክትም። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡1
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር
#አገልግሎት #መዋረድ
#መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ብፅእና #እምነት
#ታላቅነት #ማገልገል
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment