አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 14፡26
በሃጢያት ምክኒያት እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተቅበዝብዘን ነበር፡፡ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፡፡ የእግዚአብሄርን
ነገር የሚረዳ አልነበረም፡፡ በእግዚአብሄር መንገድ የሚሄድ ሰው አልነበረም፡፡
ባለመታዘዝ ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የተለያየውን የሰው ልጅን የሃጢያት እዳ ለመክፈል ኢየሱስ ወደ ምድር መጣ፡፡
በኢየሱስ ሞት የሃጢያት እዳው ሁሉ በመስቀል ላይ ስለተከፈለ ሰው በንስሃ ወደ እግዚአብሄር ሲመለስ እግዚአብሄር የራሱን መንፈስ
ይሰጠዋል፡፡ ኢየሱስን አንደ አዳኝና ጌታ ስንቀበለው የሚሰጠን መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፡፡
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄርን የመጀመሪያውን ሃሳብ ያሳየናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሰው የሃጢያት ሃሳብ ወዳልተቀላቀለው
ንፁህ የእግዚአብሄር ሃሳብ ያሳየናል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራላል፡፡
እኛ እግዚአብሄር እንዲመራን ከምንፈልገው በላይ እርሱ እኛን ሁልጊዜ ሊመራን ይፈልጋል፡፡ ለሁል ጊዜ መሪያችን ይሆን
ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል፡፡
መንፈስ ቅዱስን ለምሪታችን ፈልገነው የሚጎልብን ምንም እውነት የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ መርቶን የማንረዳውና የምንስተው
ምንም ነገር የለም፡፡ ለምሪታችን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ተደግፈን የምናጣው ብርሃን የለም፡፡
በምናደርገው በማንኛውም ውሳኔ ፈቃዱን መጠየቅ እንድንችል መንፈስ ቅዱስ መኖሪያውን በእኛ ውስጥ አድርጓል፡፡
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment