Popular Posts

Wednesday, May 31, 2017

የክርስቶስ ባህሪ - ትእግስት

በክርስትያን ህይወት ውስጥ ባህሪ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ባህሪያችን በተሰራ መጠን በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ጠቃሚነታችን ይጨምራል ለብዙዎችም በረከት እንሆናለን፡፡ ባህሪያችንን ባሳደግን መጠን ደግሞ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ያለን ተፅእኖ ይጨምራል እግዚአብሄርም ለተጨማሪ ሃላፊነት ያምነናል፡፡  
እግዚአብሄር ክብር ፈጥሮናል፡፡ እኛ የራሳችን አይደለንም፡፡ እግዚአብሄር ክብሩን ሊገልጥብን በህይወታችን በትጋት ይሰራል፡፡
አንዳንዴ የእግዚአብሄር አሰራርና የኛ አስተሳሰብ አንድ ላይሆን ይችላል፡፡ መታገስ እና እግዚአብሄርን መጠበቅ የሚያስፈልገው የእግዚአብሄር አሰራርና የእኛ ፍላጎት ሁልጊዜ አብሮ ላይሄድ ስለሚችል ነው፡፡
የእግዚአብሄርን እውነተኛውን ነገር ማግኘት ከፈለግን እግዚአብሄርን መከተል አለብን ሌላ መንገድ የለውም፡፡ እግዚአብሄር የራሱ እርምጃ አለው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ፍጥነት አይገባም፡፡ ስለዚህ ነው ከእግዚአብሄር ጋር በትህትና ለመኖርና ለማፍራት ትእግስት ወሳኝ የሚሆነው፡፡
የእግዚአብሄርን እርምጃ ሳንጠብቅ የምናደርገው ነገር የእኛ እንጂ የእርሱ አይሆንም፡፡
በህይወታችን እግዚአብሄርን ብቻ ሳይሆን ሰውንም መታገስ ይገባናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ደረጃ እና አመለካከት አለው፡፡ ከሰው ጋር አብሮ ለመኖርና ለማገልገል በዚያም ፍሬያማ ለመሆን ትግስት ይጠይቃል፡፡ ሰው ሁሉ እኛን ይምሰል ማለት ትእቢት ነው፡፡ ሰውን መታገስ ግን ትህትና ነው፡፡
ማንኛውም ሃይል ካለመቆጣጠሪያ መሳሪያው አደገኛ እንደሆነ ሁሉ ባህሪው ያልተሰራ ሰው አደገኛ ነው፡፡ ባህሪው ያላደገ ሰው  ራሱን ተቆጣጥሮ ሃይሉን በምን ላይ ማፍሰስ እንዳለበት አያውቅም፡፡ ለዚህ ነው ከሃይል ይልቅ ባህሪ ይበልጣል የሚባለው፡፡
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16፡32
በህይወታችን ልናሳድገው የሚገባን ባህሪ ትግስት ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን በትጋት እየሰራ ያለው ትእግስትን ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ሮሜ 5፡3-4
ካለ ትእግስት ግን ምንም ነገር ቢኖረን ከንቱ ነው፡፡ ትእግስት ሙሉ እና ፍፁም ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀን ፍፁም ሰዎች ያደርገናል፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ያዕቆብ 12-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

Tuesday, May 30, 2017

የባህሪ ውበት

እግዚአብሄር የፈጠረን በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄርን በምድር ላይ የፈጠረን በባህሪው እግዚአብሄርን በምድር ላይ እንድንወክለው ነው፡፡   
እግዚአብሄር በኢየሱስ የመስቀል ስራ የሃጢያት እዳችንን ሁሉ ሲከፍል እንደገና ልጆቹ እንድንሆንና ይእግዚአብሄርን ባህሪ በምድር ላይ እንድናንፀባርቅ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ቤተሰብ ተቀባይነት አግኝተናል፡፡ በባህሪ ስናድግ ደግሞ እግዚአብሄርን በሙላት እንወክለዋለን፡፡ የህፃንነትን ባህሪ ሽረን በክርስቶስ ባህሪ ስንገለጥ ለብዙዎች በረከት እንሆናለን፡፡
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡11
እግዚአብሄር ደግሞ የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠንን ነገር አንድናባክነው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ዘይቱን ካፍሰሱ በፊትር ዘይቱ የሚቀመጥበትን ሸክላ መስራት ማደስ ቀዳዳውን መድፈን ይፈልጋል፡፡ የተሰነጠቀና በሚያፈስ እቃ ዘይት ቢጨመርበት ለተፈለገው ያህል ጊዜ ቆይቶ ሊጠውቅም አይችልም፡፡ የተሰነጠቀና የሚያፈስ እቃ ዘይት ቢጨመርበትም ያባክናል፡፡  
እግዚአብሄር ለእኛ ስጦታን ለመስጠት ሰከንድ አይፈጅበትም፡፡ እኛ ግን ባህሪያችንን ለመስራትና በክርስቶስ ባህሪ ለማደግ ወራትና አመታት ይፈጅብናል፡፡  
በክርስቶስ ባህሪ ብዙዎችን እንድንደርስና ለብዙዎች በረከት እንድንሆን ባህሪያችንን የሚሰሩትን ሂደቶች ደስ መሰኘትና መታገስ ይኖርብናል፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ሮሜ 5፡3-4
ከእግዚአብሄር በምናገኘው በረከትና መጨመር ብቻ ሳይሆን በምናስተዳድርበትን ባህሪ መጎልበት ላይ ማተኮር ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር አስተዳዳሪው ሳይሰራ ንብረቱን መስጠት አይፈልግም፡፡ አስተዳዳሪው ሃብቱን የሚጠብቅበት ባህሪ ሳይኖረው ሃብቱ ቢመጣ ከንቱ ነው፡፡
የንጉስ ልጅ ምንም የንጉስ ቤተሰብ ቢሆን ንብረቱን በሚገባ ለማስተዳደር እስኪያድግ ይጠበቃል፡፡ ያላደገ ልጅ ማስተዳደር አይችልም፡፡
ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ገላትያ 4፡1-2
የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እኛ ይበልጥ እንድናገለግለውና ተጨማሪ ሃላፊነቶች እንዲሰጠን ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር ተጨማሪ ሃላፊነቶች ሊሰጠን በባህሪያችን እስክናድግ እየጠበቀ ነው፡፡ እግዚአብሄር በባህሪያችን ላይ በትጋት እየሰራ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር አሰራር ጋር ተባብረን ለብዙዎች በረከት ለመሆን እንሰራ፡፡እንደባህሪ መሰራት ለተጠራንለት ጥሪ ፍፁም የሚያደርግ ነገር የለም፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ያዕቆብ 1፡2-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

እግዚአብሄር ልብን አይቶ ያደላል

እግዚአብሄር የሰውን ፊትን አይቶ አያዳላም፡፡ የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት እግዚአብሄር ሰውን በውጫዊ ነገር በአነጋገሩንና በአለባበሱ አይመዝንም ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ንጉስን ሊመርጥ ሲል ለንጉስነት የሚቀባው ነቢይ የሰውን ፊት ያይ ስለነበረ ቁመታቸው ዘለግ ያለውን ሰዎች ለንጉስንት ሊቀባ ነበር፡፡
እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 16፡6-7
እግዚአብሄር ሰው እንደሚያይ አያይም ፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ በውጭ በሚያየው ውስን ይሆናል፡፡ ሰው ማየት የሚችለው ፊትን ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችልው የውጫዊውን ገፅታ ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችለው የሰውን ልብስ እና የሚነዳውን መኪና ነው፡፡ ሰው ሰውን የሚመዝነው በውጫዊ ማየት በሚችልው በውጫዊ ነገር ብቻ ነው፡፡
ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ። ሐዋርያት 10፡34-35
ሰው እንደሚያይ እግዚአብሄር አያይም፡፡ እግዚአብሄር የሰው መመዘኛ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ከልብስና ከውጫዊ ገፅታ ባሻገር የሰውን ዋናውን ነገር ልብን ማየት ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰው ያከበረውን እግዚአብሄር ሊንቀው ይችላል፡፡ ሰው የናቀውን ደግሞ እግዚአብሄር ሊያከብረው ይችላል፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና። ሮሜ 2፡11
እውነት ነው እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ ይህ ማለት ግን እግዚአብሄር አይመዝንም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት ግን እግዚአብሄር መመዘኛ የለውም ማለት አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የራሱ መመዘኛ አለው፡፡ የእግዚአብሄር መመዘኛ እንደ ሰው መመዘኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፊትን እይቶ አያዳላም እንጂ እግዚአብሄር ግን የራሱ ምርጫ አለው፡፡ እግዚአብሄር ይመርጣል፡፡ እግዚአብሄር የሚመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር የማይመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው ስው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የማያስደስተው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያዘነብላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው አያዘነብልም፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያደላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው ደግሞ አያደላም፡፡ እግዚአብሄር ግን ያደላል፡፡
እግዚአብሄር ፊትን አይቶ አያዳላም እንጂ ልብን አይቶ ግን ያደላል፡፡ እግዚአብሄር የሰው ልብ ይማርከዋል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ልብ ይመዝናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የልብ አይነት አለ፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
እግዚአብሄር ልብን አይቶ ማድላት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፍፁም ልብ ባለው ሰው ህይወት ሃይሉን ለመግለጥ ፈልጎ አይኖቹ በምድር ላይ ይመላለሳሉ፡፡  
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። 2ኛ ዜና 16፡9
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሚለው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 3፡5፣ 4፡23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ልብ #ዋጋ # #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Monday, May 29, 2017

የፀጋ ቃል

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ኤፌሶን 4፡29
ፀጋ የሚያስችል ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ፀጋ የሚያስችል ሃይል ነው፡፡ ፀጋ የሚያበቃ ችሎታ ነው፡፡ ፀጋ የሚያስችል ሃይል ነው፡፡ እንደ ክርስቲያን የፀጋ ቃል ብቻ ከአፋችንም እንዲወጣ ታዘናል፡፡
እግዚአብሄር በመንፈሱ በተለያየ ፀጋ አሳድጎናል፡፡ እግዚአብሄር በፀጋው ለውጦናል፡፡ እግዚአብሄር በፀጋው ካለንበት አውጥቶናል፡፡ በፀጋው ከብዙ ነገር አሻግሮናል፡፡  
እግዚአብሄር በቃላችን ውስጥ ታላቅ ሃይልን አስቀምጧል፡፡ እኛ ውስጥ የተጠራቀመው ፀጋ በቃላችን በኩል ሌሎችን በህይወታቸው ካለው ነገር እንዲያወጣቸው ያስፈልጋል፡፡ በቃላችን ውስጥ ያለው ፀጋ መንፈሳዊ ጉልበትን የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡ የሚሰሙን በቃላችን በኩል የእግዚአብሄርን ፀጋ ይመገባሉ፡፡ እኛን ያበረታን ፀጋ በቃላችን በኩል ለሌሎች ይተላለፋል፡፡ የሆነውን የሆንበትን ፀጋን ለሌሎች ማካፈል እንችላለን፡፡      
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ኤፌሶን 4፡29
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ንግግር #ቃል #አንደበት #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ


Sunday, May 28, 2017

የመንፈስ ፍሬዎች

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ ውስጠኛው ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን መስሎ ነው ፡፡  
እግዚአብሄር ላይ ባመፀ ጊዜ ሰው መንፈስ ከእግዚአብሄር ተለየ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው የአባትና የልጅ ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚመስልበት መልኩ ጠፋ፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ህይወት ፍሬ የነበረውን ፅድቅ ሰላም ደስታ ፍቅር በጎነት የመሳሰሉትን ባህሪ አጣ፡፡
ሰው እግዚአብሄርን ባለመታዘዝ በሰይጣን ግዛት ውስጥ ከወደቀ በኋላ እነዚህን የመንፈስ ፍሬዎች ሁሉ አጣ፡፡ ከእውነተኛው የህይወት ምንጭ ጋር ስለተለያየ እነዚህን የመንፈስ ፍሬዎች ማፍራት ተሳነው፡፡ ከመልካምነት ግንድ ላይ ተቆርጦና ተለያይቶ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ቅርንጫፍ የለም፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም። ያዕቆብ 3፡12
ክርስትና እውነተኛ ህይወት ነው፡፡ ካለ እግዚአብሄር እውነተኛን ፍሬ ማፍራት መሞከር ልፋት ነው፡፡
በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና፡፡ ዮሐንስ 15፡4-5
ሰው የተጠራው እግዚአብሄርን ለመምሰል ነው፡፡ ሰው በኢየሱስ አዳኝነት ሲያምን ዳግመኛ ይወለዳል፡፡ ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ሲቀበል መንፈሱ ህይወት ይዘራል፡፡ ህይወት ያለው ነገር ደግሞ አድጎ ፍሬ ማፍራቱ አይቀርም፡፡  
አሁንም እግዚአብሄርን መምሰል የምንችለው በባህሪያችን ፍሬ ነው፡፡ ከእውነተኛ ህይወት ጋር መገናኘታችን የሚታወቀው የመንፈስ ፍሬ በህይወታችን ሲታይ ነው፡፡  
በክርስቶስ የእግዚአብሄርን ቃል ስንታዘዝ ፍሬን ማፍራት እንጀምራለን፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል አብዝተን በታዘዝን ቁጥር የመንፈስን ፍሬ በህይወታችን ይበዛል፡፡
ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሐንስ 15፡5
የእግዚአብሄር ህይወት እንዳለንና ህይወታችን እያደገ እንደሆነ የሚታየው የእግዚአብሄር ባህሪ የሆኑትን የመንፈስ ፍሬዎች ስናፈራና ፍሬዎቻችንም ሲበዙ ነው፡፡  
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። ገላትያ 5፡22
ክርስትና እውነተኛ ህይወት ነው፡፡ የመንፈስን ፍሬ አብዝተን ባፈራን መጠን ሰዎች ይህንን እውነተኛ ፍሬ ለመጠቀም ወደ እኛ ይሳባሉ፡፡ የመንፈስ ፍሬ በህይወታችን በታየ መጠን ሰዎች እኛን መሆን ይፈልጋሉ እንዲሁም እኛ የምንከተለውን ጌታ ኢየሱስን መከተል ይፈልጋሉ፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

የአገልግሎት ስምረት መለኪያ

የቃል አገልጋይ ስኬት የሚለካው ክርስቶስን በመስበክ በክርስቶስ ፍፁም የሆነን ሰው በማቅረብ ነው ፡፡
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ። ቆላስይስ 1፡28-29
የቃል አገልግሎት ስኬት የሚለካው ሰዎችን ምን ያህል ወደ ክርስቶስ እንዲያድጉ በመደረጉ ነው፡፡
ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤ ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል። ኤፌሶን 4፡15-16
የእግዚአብሄር ቃል አገልግሎት ስምረት የሚለካው ሰዎች ምን ያህል በክርስቶስ ፍቅር መኖር መማራቸው ነው፡፡
ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም። የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡4-5
የቃል አገልጋይ ስኬት የሚመዘነው የተሰቀለውን ክርስቶስን በሰዎች አይን ፊት በግልፅ መሳሉ ነው፡፡
የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?ገላትያ ሰዎች 3፡1
የእግዚአብሄር ቃል አገልጋይ የሚመዘነው በሰዎች ልብ ክርስቶስን መፃፉ ነው፡፡
እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3:1-3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

Saturday, May 27, 2017

ሰዎችን አጥማጆች

እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ማቴዎስ 4፡19
ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያታችንን እዳ በመክፈሉ የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ አይኖርም፡፡ ኢየሱስን አዳኛችንና ጌታችን አድርገን በመቀበላችን ከጥፋት ድነናል የዘላለም ህይወት አግኝተናል፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
ሰዎችን የማጥመድ ታላቅ ሃላፊነት ባይኖርብን ኖሮ ወዲያው እንደዳንን እግዚአብሄር በሰበሰበንና በዚህም ምድር እንድኖር ባልፈለገ ነበር፡፡ በዚህ ምድር የቆየነው ሌሎችን የማጥመድ ሃላፊነትን ተሸክመን ነው፡፡
በምድር ላይ ስንኖር ይህን ሰዎችን የማጥመድ አላማን ይዘን ነው የምንኖረው፡፡ በምድር የምንኖረው ይህንን ሰዎችን የማጥመድ ሸክም ተሸክመን ነው፡፡ በምድር የምንኖረው በአስተሳሰባችን በአነጋገራችንና በአደራረጋችን ይህንን ታላቅ ተልእኮ ለማሳካት ነው፡፡
ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡ 10-12
በውጭ ካሉት ጋር ስንኖር አነጋጋራችንና አካሄዳችን እነርሱን ለክርስቶስ ለማጥመድ ንስሃ እንዲገቡና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁ የታቀደ መሆን ይገባዋል፡፡
ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን። ቆላስይስ 4፡5-6
ራሳችንን በመግዛት ፣ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ በማመስገንና ባለማጉረምረም በአለም እንደ ብርሃን እየታየን ብዙዎችን የማጥመድ እድል በእጃችን ነው፡፡
በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-16
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #አጥማጆች #ብርሃን #ጨው #ምስክር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

Friday, May 26, 2017

የመኖሪያ ፈቃድ

እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲግባባ ነው፡፡ ሰው በምድር ላይ የእግዚአብሄርን አላማ እንዲያስፈፅም በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ተፈጥሮአል፡፡
ሰው ሃጢያት በሰራና በእግዚአብሄር ላይ ባመፀ ጊዜ ከእግዚአብሄ ጋር የነበረው የአባትና ልጅ ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መግባባት አቃተው፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ እውነትን አጣው፡፡
ኢየሱስ ወደምድር የመጣውና የሃጢያት እዳችንን ሁሉ የከፈለው የእግዚአብሄር ልጆች እንድንሆንና የእግዚአብሄር መንፈስ እንዲያድርብንና ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራን ነው፡፡    
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20፣27
የእግዚአብሄር መንፈስ ለጥቂት ሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ በጌታ ኢየሱስ ያመነ ሰው ሁሉ ከቅዱሱ ቅባት ተቀብሎዋል፡፡ በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላችን የእግዚአብሄር ምሪት ስለሚያስፈልገን ይህ የተቀበልነው ቅባት በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16
ይህ በእኛ ውስጥ ለዘላለም የሚኖረው ቅባት የእግዚአብሄርን መንገድ ያስተምረናል፡፡
ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ዮሃንስ 16፡13
ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ዮሐንስ 14፡15-17
አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።ዮሐንስ 14፡26
እከሌ ካላስተማረኝ ዋጋ የለኝም እስከማንል ድረስ ወይም ግዴታ ሌላ አስተማሪ ሊያስተምረን እስከማያስፈልገን ድረስ ቅባቱ በህይወታችን ማወቅ ያለብንን ነገር ሁሉ ያስተምረናል፡፡
በውስጣችን የሚኖረው ቅባት የሚያስተምረን አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳይሆን ዘወትር ያስተምረናል፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ከየት አገኘዋለሁ እሰከማንል ድረስ የእግዚአብሄር እውነት በቅባቱ በልባችን ቀርቦዋል፡፡
ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ሮሜ 10፡6-7
ይህ በውስጣችን ያለው ቅባት የሚያስተምረን ስለሁሉ ነው፡፡ በህይወታችን ያለውን ሃላፊነት የምንወጣበትን እውቀት ሁሉ ይሰጠናል፡፡ ይህ ትንሽ ነው ብሎ የሚንቀውና የማያስተምረን ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ከምናስበው በላይ ስለህይወት ዝርዝር ነገራችን እንደሚገደው ሁሉ  በውስጣችን ያለው ቅባት ስለዝርዝር ነገራችን ሁሉ ያስተምረናል፡፡ ማቴዎስ 10፡30
ይህ ቅባት የሚያስተምረው ነገር ሁሉ አስተማማኝ እውነት ነው፡፡ በሌላ በማንም ባትተማመኑ በውስጣችሁ ቅባት መተማመን አለባችሁ፡፡ ማንም ቢዋሽ ይህ ቅባት እውነተኛውን ነገር ይናገራል፡፡
እንዳስተማረን በእርሱ ልንኖር ይገባናል፡፡ በሌላ በምንም ለመኖር ብንፈራ ቅባቱ ባስተማረን ለመኖርት መፍራት የለብን፡፡ ሌላ ምንም ያስተናል ብንል ብንጠራጠር ቅባቱ ግን አያስተንም፡፡ በሌላ በምንም እውቀት ለመኖር ነፃነቱ ባይኖረን ቅባቱ እንዳስተማረን ለመኖር ግን ነፃነቱ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ በቅባቱ ምሪት ነፃ ካልሆንን በምንም ነፃ አንሆንም፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20፣27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #እውነት #ምሪት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት  #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Thursday, May 25, 2017

እምነት ሲገለጥ


እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1
የሚታይ አለምን አለ የማይታይ አለም አለ፡፡ እምነት የማይታየው አለም ውስጥ ምን እየተሰራ እንደሆነ የምናይበትና መንገድ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮአዊ አይናችን የማይታየው አለም ውስጥ ምን እንዳለ በመንፈሳዊ አይናችን አይተን የምናረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡
ይህ የምንኖርበት አለም ያልነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህ የምንኖርበት አለም እንኳን የመጣው ከማይታየው አለም ነው፡፡ አለም የተፈጠረው በማይታየው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡   
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3
ሰው ካላየ ማረጋገጥ አይችልም፡፡ የምናየውን እንዳለ እርግጠኛ እንሆናለን፡፡ እምነት የሚያስረግጥ ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር በመንፈሳዊ አለም እንዳለ የሚያረጋገጥልን ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር የምናይበት መንገድ ነው፡፡ እምነት በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን የማንደርስበትን አለም የሚያይና ምን እንዳለ የሚያረጋግጥልን ነገር ነው፡፡
እምነት ከሚታየው አለም አልፎ የማይታየውን ዘላለማዊውን አለም የምናይበትና የምናረጋግጥበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17
አሁን ያለን ማንኛውም እውቀት ሁሉ የመጣው ካስረዳን ሰው ነው፡፡ እምነት የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ እምነት የሚታየው አለም ሁሉ ምንጭ በሆነው በመንፈሳዊ አለም ያለውን ነገር አይቶ የሚያስተምረን የሚያስረዳን አስረጂ ነው፡፡ እምነት የመንፈሳዊውን አለም እውቀት የሚሰጠን አስተማሪ ነው፡፡
የማይታየውን አለም የምናይበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንረዳ መንፈሳዊውን አለም እንረዳለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ የማይታየውን አለም እንሰማለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናይ የማይታየውን አለም እናያለን፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ተስፋ #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

Wednesday, May 24, 2017

40 የእምነት ጥቅሞች (ክፍል አንድ) ዕብራውያን 11፡1-20

እምነት በተፈጥሮአዊ አይናችን የማናየውን ተስፋ ለማስረገጥ ይጠቅማል፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1
እምነት እውነተኛ የእግዚአብሄር ምስክርነት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዕብራውያን 11፡2
የአለምን አጀማመር አፈጣጠር የምንረዳው በእምነት ብቻ ነው ፡፡ የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው መንፈሳዊ አለም እንደመጣ ለመረዳት እምነት ወሳኝ ነው፡፡
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።ዕብራውያን 11፡3
እግዚአብሄር የሚቀበለውን መስዋእት የምናቀርበው በእምነት ነው፡፡ 
አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።ዕብራውያን 11፡4
ከተፈጥሮአዊ ነገር በላይ ከፍ ብለን በተፈጥሮአዊ ነገር ሳንያዝና ሳንወሰን እንድንኖር የሚያደርገን እምነት ብቻ ነው፡፡
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ዕብራውያን 11፡5
እምነት ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሰምርና ጌታን ለማስደሰት ይጠቅማል፡፡ እምነት ከእግዚአብሄር ዋጋን ያሰጠናል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።ዕብራውያን 11፡6
እምነት በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነትን ይሰጠናል፡፡
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። ዕብራውያን 11፡7
በምንም ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሄርን እንድንታዘዝ እምነት ይጠቅማል፡፡
አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ዕብራውያን 11፡8
እምነት የተስፋ ቃላችንን በመመልከት የዛሬን መከራ እንድንንቅና እንድንታገስ ያደርገናል፡፡
ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ ዕብራውያን 11፡9
እምነት የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል በትግስት እንድንጠብቅ ጉልበት ይሆነናል፡፡
መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።ዕብራውያን 11፡10
እምነት የማይቻል ነገር እንድናደርግ ከተፈጥሮ በላይ የሆነን አቅምን ይሰጠናል፡፡
ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ዕብራውያን 11፡11
እምነት ከሞተ ነገር ውስጥ ህይወት እንዲወጣና እንዲበዛ ያስችላል፡፡
ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። ዕብራውያን 11፡12
እምነት በዚህ አለም እንግዳ ሆነን እንድንኖር ያስችለናል፡
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። ዕብራውያን 11፡13
እምነት ከእግዚአብሄር የሆነውን እውነተኛውን ነገር እንድንፈልግ ያፀናናል፡፡
እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤  ዕብራውያን 11፡14-15
እምነት ልባችን መዝገባችን ባለበት በሰማይ እንዲሆን ያስችላል፡፡  
አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ዕብራውያን 11፡16
እምነት ከእኛ ችሎታ ያለፈ መስዋእትን እንድናቀርብና ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡
አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤ ዕብራውያን 11፡17-18
እምነት እግዚአብሄር ለሞተው ህይወትን እንደሚሰጥ በማመን ከሞት በላይ እንድናስብ ይጠቅመናል፡፡
እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው።ዕብራውያን 11፡19
እምነት የእግዚአብሄርን በረከት በሌሎች ላይ እንድናስተላልፍ ያስችለናል፡፡
ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው። ዕብራውያን 11፡20
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ