Popular Posts

Tuesday, September 6, 2016

እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ!

ሰዎችን የሚማርኳቸውና የሚደሰቱባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ካለ እምነት ግን እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራዊያን 116

እምነት ደግሞ መንፈሳዊውን አለም ማየትና በዚያው መመላለስ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮአዊ አይን ከሚታየው አለም ባለፈ የመንፈሳዊውን አለም ማየትና ከመንፈሳዊ አለም ጋር አብሮ መራመድ ነው፡፡ እምነት በአካባቢያችን ከምናየው ነገር በላይ የእግዚአብሄርን ቃል ማየትና እንደ እግዚአብሄር ቃል መመላለስ ነው፡፡  

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 111

  • ·         እምነትም የሚመጣበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት እንደሆነ አውቀን የእግዚአብሄርን ቃል በጥንቃቄ መስማት ይገባናል፡፡


እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 1017

የእግዚአብሄርን ቃል አሰማማችን በውስጣችን እምነት እንዲፈጠር ወይም እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ሰው ቃል ካለሰማነው የእግዚአብሄር ቃል እንደእግዚአበሄ ቃል በእምነትና በየዋህነት ከተቀበልነው በውስጣችን እምነትን ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ነው እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ የሚለው፡፡ /ሉቃስ 8:18/

  • ·         ቃሉን አሰማማችን ፍሬ እስከምናገኝበት ድረስ በቃሉ ለመፅናት መሆን አለበት፡፡  


በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። ሉቃስ 815

በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል። ማቴዎስ 1323

  • ·         ቃሉን አማራጭ የሌለው ብቸኛ መፍትሄ እንደሆነ በማመን ወደቃሉ መምጣትና ቃሉን መስማት አለብን፡፡


ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ። ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ ዮሃንስ 667-68

  • ·         የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ ለመፈወስና ለመለወጥ ተዘጋጅተን በመጠባበቅ መሆን አለበት፡፡


ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ሉቃስ 617

  • ·         የእግዚአብሄር ቃል ህያው እደሆነና ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ውስጣችንን ሊለውጥ እንደሚችል በማወቅ በአክብሮት ልንሰማው ይገባናል


የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ሮሜ 4፡12

የእግዚአብሄርን ቃል እንደሚሰራና እንደሚለውጥ ቃል ካልተቀበልነው በህይወታችን ሊሰራናየምንፈልገውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡  

ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ዕብራውያን 4፡2

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ



#ቃል  #እምነት #መንፈስ #መፅሃፍቅዱስ #ነፍስ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት#አማርኛ #ስብከት #መዳን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment