Popular Posts

Saturday, February 4, 2017

የመጨረሻው እድል

እግዚአብሄር ሰውን ፈጥሮአል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ሃጢያትና ድካም ይረዳል፡፡
እግዚአብሄር ግን የማይቀበለውና ምንም ሰበብ የማይቀበልበት አንድ ሃጢያት አለ፡፡ ሰው ምንም ያህል ምክኒያት ቢያቀርብ ተቀባይነት የማይኖረው አንድ አመፃ አለ፡፡ ይህ ሃጢያት በእግዚአብሄር ፊት ምንም ሰበብ ተቀባይነት የማይኖረው ነው፡፡
በሃጢያት ምክኒያት ሰውና እግዚአብሄር ተጣልተው ነበር፡፡ በሰው አመፅ ምክኒያት ሰውና እግዚአብሄር ጠላቶች ነበሩ፡፡ የሰው ልጅ ከሚጠፋ የመታረቂያውን መንገድ እራሱ እግዚአብሄር አዘጋጀ፡፡ ሰው ሁሉ ወደ መዳን አንዲደርስ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 116
ስለሰዎች ሃጢያት እንዲሞት እግዚአብሄር አንድያ ልጁን ኢየሱስን ወደ አለም ልኮታል፡፡ ኢየሱስ በእኛ ምትክ ሆኖ እኛ መሰቃየት የነበረብንን ስቃይ ተሰቃይቷል፡፡ እኛ መሞት የነበረብንን ሞት በመሞት ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ከፍሎልናል፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 336
ስለሰው ሃጢያት እግዚአብሄር ይህን ሁሉ አዘጋጅቶ ሰውን ይቅር ለማለት እየጠበቀ ሰው ግን ይህንን ባይቀበል ከዚህ በላይ መስዋእት ሊደረግለት አይቻልም፡፡ ሰው እንዳይጠፋ ያዘጋጀለትን የደህንንት መንገድ ካልተቀበለ እግዚአብሄር ካለፈቃዱ በግድ ሊያድነው አይችልም፡፡ 
ሰው ኢየሱስን በመቀበል ከእግዚአብሄር ጋር ታርቆ የእግዚአብሄር ልጅ መሆን ካልፈለገ እግዚአብሄር ምንም ሊያደርግለት አይችልም፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 112
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡3
ይህን ኢየሱስን መቀበል የሚፈልግ ማንም ሰው ይህን ፀሎት አብሮኝ መፀለይ ይችላል፡፡
ፀሎት
እግዚአብሄር ሆይ ስላዘጋጀህልኝ የመዳኛ መንገድ ልጅህን ኢየሱስን ስለላክልኝና አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ የሃጢያቴን እዳ ለመክፈል እንደሞተና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን የህይወቴ አዳኝና ጌታ አድርጌ በህይወቴ ላይ እሾመዋለሁ፡፡  
እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን   
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment