ፍቅር ስግብግብ አይደለም፡፡ ፍቅር ስቁንቁን አይደለም፡፡ ፍቅር ቋጣሪ አይደለም፡፡ ፍቅር ራስ ወዳድ አይደለም፡፡ ፍቅር ስስታም አይደለም፡፡ ፍቅር ጨካኝ አይደለም፡፡ ፍቅር
ርህሩህ ነው፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር
አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
ፍቅር ቸር ነው፡፡ ፍቅር ለጋስ ነው፡፡ ፍቅር መሃሪ ነው፡፡ ፍቅር ይቅር ባይ ነው፡፡
ፍቅር ትግስተኛ ነው፡፡ ፍቅር መልካም አሳቢ ነው፡፡ ፍቅር ደግ ነው፡፡ ፍቅር ለሁሉም ይራራል፡፡
ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤
የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና። ሉቃስ 14፡13-14
ፍቅር ይባርካል፡፡ ፍቅር ይለቃል፡፡ ፍቅር ያከብራል፡፡ ፍቅር ይለግሳል፡፡ ፍቅር
ይሰጣል፡፡ ፍቅር ያካፍላል፡፡ ፍቅር ከሌላው ምንም ተስፋ ሳያደርግ ይባርካል፡፡
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥
ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና። አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች
ሁኑ። አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ። ሉቃስ 6፥35፣36
ፍቅር ማገልገል ስለሚወድ ብቻ ያገለግላል፡፡ ፍቅር ማንሳት ስለሚወድ ብቻ ሰውን
ያስነሳል፡፡ ፍቅር የሰዎች ከፍታ ስለሚያስደስተው ስለሌሎች መነሳትና ከፍታ ይሰራል፡፡ ፍቅር በሌሎች ህይወት ላይ ዋጋን ይጨምራል፡፡
ፍቅር ሌሎች ሲነሱ ፣ ሲያብቡና ከፍ ሲሉ ይደሰታል፡፡ ፍቅር በሌሎች ማሸነፍና መሻገር ይረካል፡፡
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥
የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥
በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ማቴዎስ 5፡44-45
ፍቅር ሁሌ የሚሰጠው አለው፡፡ ፍቅር ሁሌ ይቅር የሚልበት አቅም አለው፡፡ በተበደለ
መጠን ፍቅር ዘወትር ምህረት የሚያደርግበት ጉልበት አለው፡፡ ፍቅር ሁልጊዜ ይቅር የሚልበት የይቅርታ ክምችት አለው፡፡ ፍቅር ሁሌ
የሚሰጠው አያጣም፡፡ ፍቅር ሁሌ የሚያካፍለው አለው፡፡ ፍቅር ሰጥቶ አይጠግብም፡፡ ፍቅር አካፍሎ አይጎድልም፡፡
ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4
ፍቅር ራሱን ያውቃል፡፡ ፍቅር የረካ ነው፡፡ ፍቅር ከውድድር ነፃ የወጣ ነው፡፡
ፍቅር ከፉክክር ነፃ ነው፡፡ ፍቅር ተልእኮው ልዩ ስለሆነ ከማንም ጋር አይወዳደርም፡፡ ፍቅር ሊያጎድለው የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ
ያውቃል፡፡ ፍቅር ደሃ ሊያደርገው የሚችል ሃይል እንደሌለ ያምናል፡፡ ፍቅር ሃብቱን በልቶ የሚጨርስ ሰው እንደሌለ ያምናል፡፡ ፍቅር
እጅግ በጣም ከመክበሩ የተነሳ ሊያዋርደው የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡
ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም
እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም
እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ዮሃንስ 13፡3-5
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment