Popular Posts

Friday, February 10, 2017

የማያቋርጥ የፍቅር ምንጭ

ፍቅር እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡  ሰው ለፍቅር ተፈጥሯል፡፡ የሰውን ህይወት የሚያጣፈጠው ፍቅር ነው፡፡  ለሰው ውበትን የሚሰጠው ፍቅር ነው፡፡ ለሰው ጣእምን የሚሰጠው ፍቅር ነው፡፡ ለሰው ሞገስን የሚሰጠው ፍቅር ነው፡፡ ለሰው እረፍትን የሚሰጠው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሰው በህይወቱ እውነተኛን እርካታን የሚያየው በፍቅር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰውን የሚያሳድገው ፍቅር ነው፡፡ ሰው የሚከናወነው በፍቅር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚለቀቀው በፍቅር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰው ነፃ የሚወጣው በፍቅር ሲኖር ብቻ ነው፡፡  
የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡17
ሰው ለመወደድና ለመውደድ ተፈጥሯል፡፡ ሰው ፍቅርን እንዲቀበልና እንዲሰጥ ተፈጥሯል፡፡ ሰው ፍቅርን ካልተቀበለ መስጠት አይችልም፡፡
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ፍቅርን የምንማርበት ፍፁም ምሳሌያችን ደግሞ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅርን ያየነው ከእግዚአብሄር ነው፡፡
ሰው በራሱ ሊወድ አቅም የለውም፡፡ እግዚአብሄር እንደወደደው የሚያምንና የሚያውቅ ሰው ብቻ ነው ሌላውን ለመውደድ አቅም የሚያገኘው፡፡ ፍቅር የሆነውን እግዚአብሄርን የማያውቅ በምንም መልኩ ፍቅርን ሊያውቅ አይችልም፡፡
እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 4፡16
ከእግዚአብሄር ፍቅርን የተቀበለና የእግዚአብሄርን ፍቅር የተረዳ ሰው ሌላውን ሊወድ ይችላል፡፡ ሰው ሰውን በእውነተኛ ፍቅር ሊወድ የሚችለው በእግዚአብሄር መወደዱን ሲረዳ ብቻ ነው፡፡ ሰው ሌላውን ሊወድ የሚችልበት መጠን እግዚአብሄር እርሱን እንዴት እንደወደደው በተረዳበት መጠን ብቻ ነው፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4፡7-8
ሰው ያልተቀበለውን ፍቅር ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሰው ባልተወደደበት መወደድ ሊወድ አይችልም፡፡ ሰው ባልተረዳው ፍቅር መውደድ አይችልም፡፡
እግዚአብሄር ምን ያህል እንደወደደው የተረዳ ሰው ሌላውን ይወዳል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር የተቀበለ ሰው ለሌላው ፍቅርን ይሰጣል፡፡ ሰው ምን ያህል እንደተወደደ በተረዳበት መጠን ብቻ ሌላውን መውደድ ይችላል፡፡
ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ማቴዎስ 18፡32-33
በተወደደው መጠን ብቻ ፣ የእግዚአብሄርን ፍቅር በተቀበለበት መጠን ብቻ ፣ የእግዚአብሄርን ፍቅር ባየበት መጠን ብቻ ፣ የእግዚአብሄርን ፍቅር ባወቀበት መጠን ብቻ ነው ሰው ሌላውን መውደድ የሚችለው፡፡ ሰውን መውደድ የሚያቅተው ሰው እግዚአብሄር እንደወደደው የማይረዳ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር እንዴት እንደወደደው ያላወቀ ሰው ሰውን እንዴት እንደሚወድ አያውቅም፡፡
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡5
ስለተወደድን መውደድ እንችላለን፡፡ ካለምክኒያት ስለተወደደን መውደድ እንችላለን፡፡ ጠላቶች ሆነን ስለተወደድን ጠላታችንን መውደድ እንችላለን፡፡ ፍቅርን ስለተቀበልን ፍቅርን መስጠት እንችላለን፡፡ በፍቅር ስለተቀበልን ፍቅርን ማመስጠት እናውቅበታለን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum...
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm...
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #መውደድ #መስጠት #መልካምነት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

    


No comments:

Post a Comment