ቃልም
ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14
አንድ
የእግዚአብሄር ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብር ያየነው በኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ልጆቹን እንዴት እንደሚያያቸው ያየነው በኢየሱስ
ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች በእግዚአብሄር ዘንድ ያላቸውን የክብር ቦታ ያየነው በክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች በአባታቸው
በእግዚአብሄር ዘንድ ያላቸውን ስልጣን ያየነው በክርስቶስ ነው፡፡ አባታቸው ልጆቹን እንዴት እንደሚወዳቸው ያየነው በኢየሱስ ነው፡፡
ኢየሱስ
የእግዚአብሄ ልጅነት ናሙና ነው፡፡ ኢየሱስ የኢየሱስ ልጅነት ክብር ሞዴል ነው፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስን እንድንመስል የተጠራነው፡፡
ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡
እኔ
ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡1
የእግዚአብሄር
ውሳኔ የእግዚአብሄር ልጆች ሁሉ ኢየሱስን እንዲመስሉ ነው፡፡
ልጁ
በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8፡29
ኢየሱስ
ምሳሌያችን ነው፡፡ ኢየሱስ የእኛን ስጋ ለብሶ በመምጣት ስጋ የለበሰ ሰው እንዴት ከሃጢያት በላይ መኖር እንደሚችል አሳይቶናል፡፡
ከሃጢያት በላይ ሆነን እንዳንኖር ምንም ሰበብ የለንም፡፡
ከኃጢአት
በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ ዕብራውያን 4፡15
ኢየሱስ
በምድር ላይ እንዳሸነፈ እኛም በሁሉ ነገር እንድናሸንፍ ኢየሱስን የምንመስልበት ሁሉም ነገር ተሰጥቶናል፡፡
የመለኮቱ
ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና
በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡2-3
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የልጅነትክብር #ናሙና #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ሞዴል #መምሰል #የእግዚአብሄርእቅድ
#የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment