እምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክኒያቱም እግዚአብሄርን ማስደሰተ የምንችለው በእምነት ስንኖር ብቻ ነው፡፡ እምነታችን እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ ካለ እምነት ደግሞ እግዚአብሄርን ለማስደሰት መሞከር ሞኝነት ነው፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
ይህ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው ነገር ምንድነው? እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘበት የእምነት ባህሪ መረዳት እግዚአብሄርን በምንም ሁኔታ ውስጥ ለማመን ይረዳናል፡፡
እምነት በተስፋ ስለሚኖር ነው
ሁሉም ሰው በአይን በሚታይ ነገር ሲኖር እምነት ግን የሚኖረው በአይን ከሚታይ ነገር ከፍ ብሎ ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያት እምነት በተስፋ እንጂ የሚኖረው በአይን በሚታይ ነገር አይደለም፡፡ እምነት የሚኖረው በአይን ከሚታየው ክልል አልፎ ነው፡፡ እምነት የሚኖረው በተስፋ ነው፡፡ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ተስፋ አድርጎ ይኖራል፡፡
በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ሮሜ 8፡24-25
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1
እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያቱ እምነት የማይታይን ነገር የሚያይ ስለሆነ ነው፡፡ እምነት የሚያየው የማይታየውን የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ነው፡፡ እምነት የሚሰማይ የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ነው፡፡ እምነት የሚያምነው የማይታየውን እግዚአብሄርን ነው፡፡
በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡21
እምነት ከሚታየው ይልቅ የማይታየውን ስለሚያስበልጥ ነው
እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ሌላው ምክኒያት እምነት የሚታየውን ስለማያይ የማይታየውን ስለሚያይ ነው፡፡ እምነት የሚያየው እግዚአብሄር በቃሉ ያለውን የማይታየውን ነው፡፡ እምነት ልቡን የሚጥለው እግዚአብሄር በተናገረው ነገር ላይ ነው፡፡ እምነት የሚከተለው ቃሉን ነው፡፡
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
እምነት የሚታየውን ስለማያይ ነው
እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያቱ እምነት ከቃሉ ጋር የማይስማማውንም ማንኛውም ሁኔታ አለማየቱ ነው፡፡ እምነት በአካባበው ያሉትን ጊዜያዊ ሁኔዎች አያይም፡፡ እምነት በዙሪያው የከበቡትን ገጠመኞች አያይም፡፡ እምነት በአካባቢው ከሚጮኸው ሁኔታ በላይ በልቡ የሚያሾከሽከውን የእግዚአብሄርን ቃል ያምናል፡፡ እምነት የሚታየውን ሁኔታ አይከተለም፡፡ እምነት እንደሁኔታው እና እነደጊዜው አይራመድም፡፡
ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ሮሜ 4፡18-19
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ተስፋ #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment