ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን እግዚአብሄር አባታችን
ነው፡፡ አባታችን ደግሞ ቃላችንን እንዲሰማ የምንፈልገውንም እንዲያደርግልን ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡ እንደ ስንናገር እንደ ልጆች
መሰማት እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሄር ጆሮውን ወደ እኛ እንዲያዘነብል እንፈልጋለን፡፡ ይህ ፍላጎታችን መልካም ፍላጎት ነው፡፡ ይህ
ፍላጎታችን ጤናማ ፍላጎት ነው፡፡
ስለዚህ ነው ኢየሱስ በቃሉ እግዚአብሄር የሰውን
ቃል የሚሰማበትን መንገድ የሚያስተምረው፡፡ እግዚአብሄር ቃላችንን መስማት እና ማድረግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን እንዲሰማ
የሚፈልግ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት መፅሃፍ ቅዱስ መንገዱን ያስተምራል፡፡ በፀሎት የጠየቀው እንዲመለስለት የሚፈልግ ሰው መጀመሪያ
እግዚአብሄር የጠየቀውን መመለስ አለበት፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሐንስ 15፡7
እግዚአብሄር ቃላችንን እንዲሰማ ካስፈለገ ቃሉን
መስማት አለብን፡፡ እግዚአብሄር ለቃላችን የዋህ መሆን ካለበት ለቃሉ የዋህ መሆን አለብን፡፡ እግዚአብሄር ቃላችንን እንዲያምን ካስፈለገ
ቃሉን ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሄር ለቃላችን ጆሮውን ማዘንበል ካለበት ለቃሉ ጆሮዋችንን ማዘንበል አለብን፡፡ እግዚአብሄር ቃላችንን
እንዲያከብር ቃሉን ማክበር ግዴታ ነው፡፡ እግዚአብሄር ቃላችንን እንዲቀበል
ቀላሉ መንገድ ቃሉን መቀበል ነው፡፡ እግዚአብሄር ቃላችንን እንዲታዘዝ እኛ ቃሉን መታዘዝ አለብን፡፡
እግዚአብሄር በቃላችን እንዲኖር በቃሉ መኖር ነው፡፡
የጠየቅነው እንዲደረግ እግዚአብሄር በቃሉ የጠየቀውን ማድረግ ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ቃል #መኖር #እምነት #መስማት
#መታዘዝ #በቃሉመኖር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment