እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን? ዓለቱን መታ፤ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፤ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን? መዝሙር 78፡19፥20
ከእግዚአብሄር ጋር መኖር እምነት ይጠይቃል፡፡
እግዚአብሄርን የምናየው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን
የምንፈልገው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምንታዘዘው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ደስ የምናሰኘው በእምነት ነው፡፡ ካለእምነት
እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር
የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡4
እስራኤላዊያን
እግዚአብሄር ያደርጋል! ብለው የተማመኑት ነገር ነበር፡፡ ችግሩ ግን እግዚአብሄር ይህንንስ ያደርጋልን? ብለው በጥርጣሬ አይን በማየት
እግዚአብሄርን አሙት፡፡
ለእግዚአብሄር
ሁሉ ይቻላል፡፡ እግዚአብሄር የማይችለው ነገር የለም፡፡
ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው። ማቴዎስ 19፡26
እግዚአብሄር
የዘላለም አምላክ ነው፡፡ አይደክምም አይታክትም ፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡28
ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር የለም፡፡
በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች። ዘፍጥረት 18፡14
ሁሉን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሄር ይችላል፡፡
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡2
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#መናገር #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ቃል
#መዳን #ማድረግ
#መስዋእት #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment