እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፡፡ ጠቢብ ጥበቡ የሆነ ነገር እንደሚያደርግለት አያስብ፡፡ ጠቢብ ጥበቡን አያጋንነው፡፡ ጠቢብ ጥበቡ ማድረግ የማይችለውን ብዙ ነገር እንዳለ ይረዳ፡፡ ጠቢብ የጥበቡን ውስንነት ይረዳ፡፡ ጠቢብ በጥበቡ ተስፋ አያድርግ፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ሞኝ ከህይወት ጎድያለሁ አይበል፡፡ ሞኝ ጥበበፃ ስላልሆነ ብቻ ምንም እንደጎደለው አያስብ፡፡ ሞኝ የህይወት ቁልፉ እንደሌለው ተስፋ አይቁረጥ፡፡ ሞኝ በሞኝነቱ አይሰማው፡፡
እግዚአብሄ እንዲህ ይላል፡፡ ሃያል በሃይሉ አይመካ፡፡ ሃያል በሃይሉ ደስ አይበለው፡፡ ሃያል በሃይሉ አይኩራራ፡፡ ሃያል የሃይሉን ውስንነት ይወቅ፡፡ ሃያል ሃይሉ የማያደርግለትን ብዙ ነገሮች ይረዳ፡፡ ሃያል በሃይሉ ውስጥ መልስ እንዳለ አያስብ፡፡ ሃያል በሃይሉ ላይ ልቡን አይጣል፡፡
በተቃራኒው ደካማው ከህይወት እንደተቆረጠ አይምሰለው፡፡ ደካማው በድካሙ አይዘን፡፡ ደካማው በድካሙ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ የሚያጣው እንዳለ አይምሰለው፡፡ ደካማው በድካሙ ድፍረቱን አይጣ፡፡
ባለጠጋም ባለጠግነቱ ውስጥ የህይወት መልስ ያለ አይምሰለው፡፡ ባለጠጋም ባለጠግነቱን አያጋነው፡፡ ባለጠጋም በባለጠግነቱ ከፍ ከፍ አይበል፡፡ ባለጋም ብልጥግናውን አያመሰግን፡፡ ባለጠጋ የብልጥግናውን ውስንነት ይረዳ፡፡ ባለጠጋ ብልጥግናው ማድረግ የማይችለውን ነገር ይወቅ፡፡ ባለጠጋው በብልጥግናው አይታመን፡፡
እንዲሁም በተቃራኒው ደሃ ከህይወት ድርሻ ወድቄያለሁ አይበል፡፡ ድሃ በድህነቱ ብቻ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ድሃ በድህነቱ የሚያጣው መልካምነት ነገር እንዳለ አይምሰለው፡፡ ድሃ በድህነት የህይወት ቁልፍ እንደሌለው አይሰማው፡፡ ደሃ በድህነቱ አይዘን፡፡
በጥበብ ውስጥ የህይወት መልስ የለም፡፡ ህይወት በጥበብ አትሰራም፡፡ ጥበብ የህይወት ቁልፍ አይደለም፡፡ ሃያልነት ምንም አያመጣም፡፡ ህይወት በሃያልነት አይደለም፡፡ ሃያልነት ህይወትን አይሰራም፡፡ ሃያል የህይወት ቁልፍ የለውም፡፡ ለህይወት ሃያልነት ወሳኝ አይደለም፡፡ ለህይወት ስኬት ባለጠግነት መልስ አይደለም፡፡ ባለጠግነት ህይወትን አያከናውንም፡፡ ባለጠጋ የህይወት ቁልፍ የለውም፡፡
የህይወት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር ጋር ብቻ ነው፡፡ ለሰው ህይወትን የሚያሳካው ጥበብ ፣ ሃይል ወይም ባለጠግነት ሳይሆን እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ካላለ ሃያል ሰው ሃይሉ ህይወትን ሊያሰምርለት አይችልም፡፡ የህይወት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር ጋር እንጂ ባለጠጋ ጋር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ካላለ በጥበብ ፣ በሃይል ወይም በባለጠግነት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡
አለምን የሚመራው እግዚአብሄር ነው፡፡ ለሰው ምህረትን የሚያደርገው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ነው ለሰው የማይገባውን መልካምነት የሚሰጠው፡፡ እግዚአብሄር ነው የሚፈርደው፡፡ቁልፉ እግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ የህይወት ቀልፍ ጠቢብም ጋር ፣ ሃያልም ጋር ባለጠጋም ጋር ሳትሆን እግዚአብሄር እጅ ነች፡፡ የሰውን ሃብት ፣ የሰውን ጥበብ ፣ የሰውን ባለጠግነት ሳያይ የሰውን ሳያዳላ በፅድቅ አለምን የሚያስተዳድረው እግዚአብሄር ነው፡፡
ይህን ያወቀ ሰው በጥበብ ላይ ልቡን አይጥልም፡፡ ይህን ያወቀ ሰው በሃይሉ አይመካም፡፡ ይህን የተረዳ ሰው በባለጠግነት ላይ ተስፋ አያደርግም፡፡ ይህን ያወቀ ሰው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ በሚያደርግ በእግዚአብሄር ይመካል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ጥበብ #ማስተዋል #መረዳት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment