Popular Posts

Sunday, February 12, 2017

የጦሩ ሜዳ

የሰው ጠላት ሰይጣን ነው፡፡ የሰይጣን ብቸኛው አላው የሰውን ህይወት መግደል ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ዮሃንስ 10፡10
ሰይጣን በኢየሱስ የመስቀል ስራ ሙሉ ለሙሉ ተሸንፏል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ነገር ግን ሰይጣን አሁንም በቀረው መሳሪያ ተጠቅሞ የጥፋት አላውን ለማስፈፀም ይተጋል፡፡ በኢየሱስ የመስቀል ስራ የተሸነፈውና ስልጣኑን ያጣው ሰይጣን አሁን ያለው ብቸኛ የማጥቂያ መንገድ ማታለል ነው፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ የሆነን ሃሳብ ወደ አእምሮዋችን በመላክ ህይወታችንን ለማጥቃት ይሞክራል፡፡ ያንን ሃሳብ ካልተቀበልው ሃሳቡ በእንጭጩ ይቀጫል፡፡ ሃሳቡን ከተቀበልነው ግን በዚያ ሃሳብ ተጠቅሞ ህይወታችንን ያጠቃል፡፡
ስለዚህ እውነተኛውና ዋናው መንፈሳዊ ውጊያ ያለው በአእምሮ ውስጥ ነው፡፡ የሰው ከሰይጣን ጋር ያለው ትንንቅ በአእምሮ ውስጥ ነው፡፡ ሰይጣን የሚተኩሰው የጦር መሳሪያ መድፍ ሳይሆን ክፉ ሃሳብ ነው፡፡ ሰይጣን የሚወረውረው ቦንብ በእግዚአብሄር እውቀት ላይ ከፍ ያለን የሰውን ሃሳብ ነው፡፡
የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡5
ጦርነቱ በአእምሮ ውስጥ ነው፡፡ ሰይጣን መማረክ የሚፈልገው ገዢ መሬት አእምሮዋችን ነው፡፡ አእምሮዋችንን ከማረከ ህይወታችንን ማርኳል፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በአእምሮዋችሁ እንዲታደስ የሚያዘን፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ አእምሮ የሰይጣን መፈንጫ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ አእምሮ የሰይጣን ህይወታችንን የማጥቂያ ቀዳዳ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
ልቡን በትጋት የማይጠብቅ ሰው ቤቱን ከፋፍቶ እንደሚተኛ ሰነፍ ሰው ነው፡፡    
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ  ምሳሌ 4፡23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #የጦርመሳሪያ #ምሽግ #አእምሮ #ሃሳብ #ማታለል #ብርቱ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment