የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው።
ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ይችላል።
ኤፌሶን 3:20 እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥
የእግዚአብሔር ለሚፀልዩት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ፍጥረቱ ላይ ያለው አላማ የፍቅር ነው።
መዝሙር 145:9 እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
1 ጢሞቴዎስ 6:17 … ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ….
እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ከእኛ በላይ ስለሚያውቅ ለእኛም የሚያደርግልን በምንፀልየው ላይ ብቻ ተወስኖ ሳይሆን ከምንለምነው ሁሉ በላይ ነው።
ማቴዎስ 6:8 … ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።
እግዚአብሔር ከአፋችን ቃል በላይ የልባችንን ጩኸት ሰምቶ ይመልሳል። እግዚአብሔር አውቀን ከፀለይነው በላይ የማናውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን ያሳየናል።
ኤርምያስ 33:3 ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።
1 ቆሮንቶስ 2:9 ነገር ግን፦ “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፡” ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው በሰውም ልብ ያልታሰበውን ጭምር ነው።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
No comments:
Post a Comment