I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ኢየሱስ በስጋ ወደምድር ከመምጣቱ በፊት ብሉይ ኪዳን ' የጉብኝት ባህል ' እና በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተደረገው አዲስ ኪዳን ግሞ ' የ መ ኖር ባህል ' ተብሎ ...
-
ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ኦሪት ዘጸአት 12:2 እውነተኛው አዲስ አመት የሚባለው ቃሉን ሰምተን ነጻ የምንወጣበትን ጊዜ ነው። እውነተኛው ዘመን መለወጫ የሚባለው ቃሉን ሰምተን በቃሉ ...
-
Video Transcript: In the far east they have something that’s call the Chinese bamboo tree. The Chinese bamboo tree takes five years to ...
-
የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው። ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ...
-
እግዚአብሄር - አባት የሁልጊዜ ነው፡፡ አባት ስሜቱን ዋጥ ያደርጋል፡፡ አባት ተለዋዋጭ ስሜቱን አይከተልም፡፡ አባት በመርህ ይመራል፡፡ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በ...
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2 የጥንቱን ...
-
የእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በመንፈስ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት እውነተኛ አገልግሎት ለማገልገል መቀጣጠሉና ግለቱ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ነገር ቢኖረው ነገር ግን ምንም መነሳሳትና መቀጣጠል ከ...
-
If you had it to do over again, you’d marry me for love Love and Let Live Love and Let Live By Dale Carnegie How To Win Friends And I...
-
በምድር ላይ ህዝብን የሚያስተዳድርና የሚገዛ መንግስት እንዳለ ሁሉ በመካከላችን የእግዚአብሄር መንግስት አለ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በአይን የማይታይ በስፍራ የማይወሰን መንግስት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ንጉ...
Wednesday, September 9, 2026
እውነተኛው የዘመን አቆጣጠር
ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ኦሪት ዘጸአት 12:2
እውነተኛው አዲስ አመት የሚባለው ቃሉን ሰምተን ነጻ የምንወጣበትን ጊዜ ነው። እውነተኛው ዘመን መለወጫ የሚባለው ቃሉን ሰምተን በቃሉ የዳንንበት ቀን ነው።
ዘጸአት ምዕራፍ 12 በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለእስራኤል ከግብፅ ነፃ በወጡበት ወቅት አዲስ ጅምር ያደረገበት ምዕራፍ ነው።
ዘጸአት 12፡2 — እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፦ «ይህ ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ።»
እስራኤላዊያን ሊያድናቸው የመጣውን የእግዚአብሄር ቃል ሰምተው ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን ቀን የወሩ መጀመሪያ ወሩን ደግሞ የአመቱ መጀምሪያ እንዲሆን ተነገራቸው።
ቀናቸውን እና ወራቸውን አንድ ብለው የጀመሩት ከነጻነታቸው ቀን ጀምረው ነው።
ዘጸአት 13፡3–4 ደግሞ ይህንን አዲስ ቀን እና አዲስ ወር ከግብፅ ነፃ ከመውጣታቸው ጋር ይገናኛል።
በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ፣ «አዲሱ ዓመት» የሚቀርበው እንደ ቀላል የቀን መቁጠሪያ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ቤዛነትና ነፃ ማውጣት የተፈጠረ አዲስ ጅምር እንደሆነ ነው።
ዛሬም እውነተኛ ነጻነት የእግዚአብሄርን ቃል ሰምተን ነጻ የምንወጣበት ነጻነት ነው።
ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። የዮሃንስ ወንጌል 8፡31፣ 32
አዲስ ዘመንም የእግዚአብሄርን ቃል ሰምተን ነጻ የወጣንበትን ቀን ነው።
እውነተኛው ዘመን መለወጫ ደግሞ የዘመን መቁጠሪያ ካላንደር ሳይሆን በእግዚአብሄር ቃል ነጻ የምትወጡበት ቀን ነው።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ የያዕቆብ መልእክት 1:25
በቃሉ ነጻ ለወጣ ሰው ጷጉሜ 5 የዘመን መለዋጫ ነው። የእግዚአብሄርን ቃል ሰምቶ ነጻ ለማይወጣበት ሰው ግን በመስከረም 1 እንኳን ዘመኑን አይለወጥም።
ስለዚህ ጥያቄው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት እና በማድረግ ዘመናችሁን ለመለወጥ ተዘጋጅታችኋል ወይስ ዘመኑ በራሱ ህይወቴን ይለወጣል ብላችሁ በከንቱ ተስፋ እያደረጋችሁ ነው ?
ህይወትን የሚለወጥ የእግዚአብሁሄር ቃል ብቻ ነው። ቀን ያው የተለመደው ተመሳሳይ ሰኞ ማክሰኞ ሮብ ሃሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ ነው። የእግዚአብሄር ቃል ህይወታችንን ካልለወጠ ቀን ህይወትን ሊለውጥ አይችልም።
አዲስ አመት ህይወታችን በእግዚአብሄር ቃል እንዲለወጥ የመንፈቅድበት አዲስ እድል እንጂ በራሱ የህይወት ለወጥ አይደለም።
መልካም አዲስ አመት መልካም አዲስ ህይወት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment